አዝ፦ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች ይኸው እስከ ዛሬ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (2x) ሙታን ሳለን ያኔ በደል የተሞላን ስንወጋው ቁስልህን ኃጥያት እየሰራን ፍቅርህ በርትቶ ነው ቁጣህን የሻረው ልበ ቅን ሆነህ ነው ክፉውን የማርከው (2x) አዝ፦ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች ይኸው እስከ ዛሬ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (2x) ተሰበረ ቀንበር ሸክም ተራገፈ ከእንግዲህ እስር የለም ሁሉ በአንተ አለፈ ከድካም በረታን ጉልበት አግኝተናል ኃይልን በምትሰጠን ባለ ድል ሆነናል (2x) አዝ፦ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች ይኸው እስከ ዛሬ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (2x) ከተጠመደብን ወጥመድ አስመለጥከን መኖሪያ ከለላ መሸሸጊያ ሆንከን ነጣቂም አይነካን ምን ድፍረት አግኝቶ ይኸው ምህረትህን አይቶ በእኛ ላይ በዝቶ (2x) አዝ፦ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች ይኸው እስከ ዛሬ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (2x) ሁሉን ቻይ ትከሻ ስንቱን አዝሎ አኑሯል የአባትነት ምክርህ ጠማማን አቅንቷል ምን ያልሆንከው አለ ለመረጥከን ለእኛ ጉያህ መግባት ቻልን ሆነን እድለኛ (2x) አዝ፦ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ አሸዋዎች እንደዚያው ምህረትህ በዝታልናለች ይኸው እስከ ዛሬ አኑራናለች ገና ታኖረናለች አሃ (4x)