Song Lyrics

ሞትን የረታ ጌታ

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል (2x) የዓለም መድኃኒት ይሄን ትሁት ቢደፋ አንገቱን ቀላል አርገውት እውር ሲያበራ ዲዳ ሲያናግር በክፉ አናት ላይ እሳት ሲጭር ተደንቀው አዩት ኧረ ይሄስ ማነው አውሎ ንፋሱን ወጀቡን የሚያዘው አዝ፦ ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል ትክክለኛ ሰራተኛ ሽንገላ የሌለበት እውነተኛ ሃሰተኞች ቢያደናብሩ ቃሉን በተንኮል ቢመነዝሩ ልቡ አይደነግጥ ምንም ቢሆን አይፈራ በአደባባይ በግልጥ አለ እየሰራ አዝ፦ ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል ያንበረከከ መተተኞችን በሰው ላይ የሚጫወቱ ጠንቋዮችን ጓዛቸውን ጥለው ፈረጠጡ በቁጣው ጅራፍ እየተቀጡ ጌታ ነን ያሉ የታል አቅማቸው ወድቀው ቀሩ እንጂ ሲነሱ አላየናቸው አዝ፦ ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል ወረት መስሏቸው የነገራቸው በሶስተኛው ቀን እነሳለሁ ሲላቸው መሳቂያ አደረጉት መሳለቂያ ምን ልታመጣ ከእንግዲህ ወዲያ የጠበቃት ቀን ደረሰችና አናወጣቸው ከሞት ተነሳና አዝ፦ ሞትን የረታ ጌታ ነው የምናመልከው የዲያቢሎስን ክፉ ሥራ ያፈረሰው አልተሸነፈም አይሸነፍም አይተነዋል አምላካችንን ንጉሣችንን ማን ይመስለዋል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection