Song Lyrics

ተቀይሯል

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x) ትርፉ ድካም ሁልጊዜ እሮሮ ስቆ ማልቀስ የዚህ ዓለም ኑሮ እዚም እዚያም ደስታ ለማግኘት ገላገለኝ ከመንከራተት አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x) አዋጥቶኛል እርሱን ማለቴ እረፍት ሆነኝ ሰላም ለቤቴ እጅ እግሬን የቆለፈ ኃጢያቴ በጣጥሶታል እስራቴን አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x) ሄድኩኝ በቃ ተከትየው መድኃኒቴን ወድጄው ሳልመለስ ፊቴን ላላዞር ወስኛለሁ በእግሩ ሥር መኖር አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x) የቀድሞ ታሪኬን ትታችሁ አውሩት የዛሬውን ባካችሁ እንዴት እንዳዳነኝ መስክሩ ይሄ ነው ድንቅና ተዓምሩ አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x) መላ ያጣ የተጨነቀ ተስፋው በምድር ላይ ያለቀ ይምጣ ምላሽ አለ ኢየሱስ ጋር አለቀልኝ ያለ የሰጋ አዝ፦ ተቀይሯል ሙሉ አድራሻዬ ከጌታ ጋር ሆኗል ውሎዬ አትፈላልጉኝ የለሁም እዚያ ስላገኘሁ የነፍሴን ማረፊያ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection