Song Lyrics

ኢየሱስ የዋሁ

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
አዝ:- ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ) ከዘለዓለም ቁጣ ከሲዖል አዳንከኝ እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ (2x) በቅጣት አለንጋ ብዙ ተገረፍኩኝ በገዛ ጥፋቴ ተጠቃሁ ቆሰልኩኝ እየተንገዳገድኩ አመጻዬ አስክሮኝ ገደል ከቶኝ ነበር ባትይዘኝ ገፍትሮኝ አዝ:- ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ) ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ የተፈጠርኩበት ምክንያቱ ገብቶኛል የመዳኔ ሚስጥር ተገልጦልኛል የአንተን አባትነት የልጅነቴን መብት በነጻ አገኘሁት የዘላለሙን ሀብት አዝ:- ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ) ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ ተታልዬ ኖርኩኝ ማንነቴ አባብሎኝ የመርጥኩት መንገድ የሚያዋጣኝ መስሎኝ ጊዜያዊው እርካታ ዓለም የምትሰጠው ላዩ ቢጣፍጥም ውስጡ ግን መርዝ አለው አዝ:- ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ) ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ እኔ የአለኝን አጥቶ ለሚንከራተተው ጽድቅ የኖረው መስሎት ለሚመጻደቀው የውስጥ አይኑ በርቶ ምነው እውነቱን ባየ ለክፋቱ ስትል እንደተሰቃየህ አዝ:- ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ) ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection