Song Lyrics

ጌታ ነው

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
አለኝ ያልኩት ሁሉ በንፋስ ሲወሰድ ከመከራው ብዛት ብቻዬን ስሰደድ ተስፋዬ ተሟጦ ምድረ በዳ ሳለሁ እጁን የዘረጋ እንግዳ ሰው አየሁኝ አዝ:- ጌታ ነው ኢየሱስ ነው ለእኔ የደረሰው (2x) ቀንበር የከበደኝ ሸግም የበዛብኝ ያየኝ ሁሉ የጠላኝ ወዳጅ የራቀብኝ ተረስቼ ማንም የት ደረሰ አይለኝ አንድ ድምጽ ሰማሁ ና ልጄ የሚለኝ አዝ:- ጌታ ነው ኢየሱስ ነው ለእኔ የደረሰው (2x) የኀጢአት ባሪያ ሆኜ ደስታ ከእኔ ርቆ ከጭንቀቴ ብዛት እኔነቴ አልቆ ሌት ተቀን ፍራቻ ኑሮ ሆኖ እሮሮ ሞቶ ወስዶኝ ነበር ኢየሱስ ባይደርስ ኖሮ አዝ:- ጌታ ነው ኢየሱስ ነው ለእኔ የደረሰው (2x) ባወራው ባወራው አያልቅም ብናገር እንዴት እንዳወጣኝ ከዚያ ከሞት አገር እድሜ ቀጥሎልኝ እስካሁን አቆየኝ ሲዖል ቤቴ ነበር አምላኬ ባያየኝ አዝ:- ጌታ ነው ኢየሱስ ነው ለእኔ የደረሰው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection