Song Lyrics

ከአንተ በላይ

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
ሰማይ ሆነ ምድር ጌታ ሆኖ የሚመለከው ስግደት የተገባው . (1) . ያለኸው ዓይናችን በራልን ማን አዳኝ እንደሆነ አየን ስምህ ክብራችን ነው የአንተ ነን አንኮራለን እውነተኛው አምላክ ለህዝቦችህ ያለህ አዝ:- ከአንተ በላይ አምላክ የለም ከአንተ በላይ (8x) ስንቱን ደፋርና ትዕቢተኛን ጥለሃል በውጊያ ሜዳ ላይ ቁጣህም ታይቶልሃል ሞኛሞኞች ሆነው ሊጣሉህ መጡ ታጥቀው የውርደት አቧራ ከደናቸው . (2) . ጀግና ነው አርሱ አሉ . (3) . ጌታቸው አዝ:- ከአንተ በላይ ጀግና የለም ከአንተ በላይ (8x) ወልደህ እንደሰው ምድረ በዳ ላይ አትጥልም እንጀራም እያለ ድንጋይ ብላ አትልም የወላጅ አንጀትህ ይንሰፈሰፍልናል ብሩካን እጆችህ ቆርሰው ይመግቡናል እንደአንተ ያለ አባት የትስ ይገኝልናል አዝ:- ከአንተ በላይ አባት የለም ከአንተ በላይ (8x) ለበሽታ ሁሉ ፍቱን መድሃኒት አለህ ሞት አፋፍ ላይ ላሉ ብቸኛ መልስ አንተ ነህ በእጆችህ ተዳሰው አፎይ ያሉ ብዙ አሉ ሌት ተቀን ከማልቀስ ክእንባ የተገላገሉ ይኸው ተፈውሰው ለክብርህ ይዘምራሉ አዝ:- ከአንተ በላይ ፈዋሽ የለም ከአንተ በላይ (8x) ሃሌሉያ በሰማይ በምድር ቢሆን እንደ አንተ ያለ ማንም የለም ጌታ ሆይ ከምድር ጫፍ እስከምድር ጫፍ ታላቁ ሥምህ የተባረከ ይሁን ሃሌሉያ(፲6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection