አዝ:- ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (2x) በአንድ ልብ አብሮ መኖርን እንለማመድ መከፋፈሉ ይበቃናል ተዉ እንዋደድ መራራቁም እየሰፋ እንዳንለያይ እንሰባሰብ እናምልክ ጌታን በአንድ ላይ አዝ:- ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (2x) በቤት ሌላ ውጪ ሌላ ሁለት ዐይነት ሰው ችላ እያልን ትዕዛዛቱን እየረሳነው ሁሌ ወተት እየተጋትን እየጫጨን ነው ዛሬ እንወስን እንለወጥ ለእርሱ እንመቸው አዝ:- ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (2x) ሲቀርቡ ሳቅ ሲርቁ ሃሜት ልማድ አድርገነው ጌታ እንዳያልፍ እንዳይሰራ እጁን ይዘነው ከአንገት በላይ ወድሃለሁ ይህም አለማድላት እውነተኛይቱን ፍቅር ወዴት አደረግናት አዝ:- ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (2x) በቃል ብቻ አኗደድ ተግባር ይጨመር ፍቅራችንን ሁሉ እንዲያውቀው እያደር ይመር እጅ ለእጅ እንያያዝ ስራም እንስራ ጠላት መግቢያ ቀዳዳ አያግኝ እኛን ሲያይ ይፍራ አዝ:- ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (2x)