Song Lyrics

ተገልብጧል ታሪክ

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
አዝ:- ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (2x) ይሄው ተራ ደርሶት ምሥጋናን ሊሰዋለት ወጣ አደባባይ ላይ ማቁ ተቀዳዶለት አከናውኖለታል ደስታው ወሰን ልክ የለው ይሄን ችግረኛ እግዚአብሔር አሰበው አዝ:- ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (2x) ተባርኮለት ጓዳው መከራውን እረሳው ታምኖበታልና ጌታው በብዙ እረዳው ምርኮው ተመለሰ የአጥፍ እጥፍ ሆነለት ካሰው ያጣውን ሁሉ እየነዳ አመጣለት አዝ:- ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (2x) ተራራ ላይ አወጣው የናቁት ሁሉ እንዲያዩት በምላስ አለንጋ ሌት ተቀን የገረፉት ሲሸላልመው አዪ በሞገስ ሲቀባባው ውስጡንም ላዩንም እንደ አበባ ሲያፈካው አዝ:- ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (2x) ቀና አለ ከአንገቱ ማቀርቀሩ ቀረና ያስተከዘው ኑሮ ድንገት ተቀየረና እነዛም ዘባቾች ሲረቱ አሉ ተደንቀው የረዳህን አምላክ እርሱን ነው የምናመልከው አዝ:- ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (2x) ተአምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection