Song Lyrics

ይመጣል

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x) ሀዘንን በደስታ ዋይታንም በሆታ ከስቃይ ገላግሎ ሊሞላ በእፎይታ ታምራቱን ሊያደርግ እጅን በአፍ ላይ ሊያስጭን ሊያስብ ምስኪኖችን አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x) ልጆቹን ሊያጽናና ሮሮዋቸውን ሊያርቅ ችግርን ሊመታ ከጭንቀት ሊያላቅቅ ለጠበቁት ጸንተው እርሱን እርሱን ላሉት ሲባረኩ ያያሉ አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x) ወጀቡን ሊገስጽ አውሎ ንፋሱንም ገስግሶ ሊመጣ ሳይፈራ ማንንም የተናጋን ኑሮ ሰላም ሊዘራበት አቤት ሲችልበት አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x) መከራም ነገ ያልፋል ችግርም ይረሳል የሚያጠግብ እንጀራ በአባት እጁ ያጐርሳል በተትረፈረፈ በሚበቃ ኑሮ ያኖራል አክብሮ አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x) እስከመቼ ድረስ እናዝናለን ላሉ ተዋረድን አጣን ተናቅን ከሰው ሁሉ ተስፋ ለቆረጡ መልካም ዜና አለው ይላል ደርሻለሁ አዝ:- ይመጣል መልስ ይዞ ይመጣል ቀን ቀጥሯል ይመጣል ኑሮን ያጣፍጣል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection