አዝ:- በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (2x) ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (2x) ቀድሞ እንደምኖረው የሞት ኑሮ አልኖርም ኃጢአት ለመቃረም ወደ ዓለም አልወርድም ጥፋት አያምረኝም መንፈሱ ገዝቶኛል ቅዱስ ደሙን ረጭቶብኝ ቅዱስ አድርጐኛል አዝ:- በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (2x) ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (2x) ሁሉን እርግፍ አድርጌ ጠቀመኝ መምጣቴ ውዴ አላሳፈረኝም ሆነኝ እረዳቴ አሁን አያይም ዓይኔ ወደ ሥጋ ለባሽ የሰው እጅ አላይም አግኝቻለሁ አጉራሽ አዝ:- በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (2x) ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (2x) ጩኸቴን ይሰማል ድምጼ ይናፍቀዋል አሸናፊው አምላኬ ድል አስለምዶኛል እምበረከካለሁ ዛሬም በጸጋው ዙፋን ስር ሲቀበር አያለሁ የተጋባኝ ችግር አዝ:- በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (2x) ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (2x) የገዛኝ ተገዛልኝ አዛዡ ሆኛለሁ ባለማዕረግ ሆንኩኝ ስልጣን አግኝቻለሁ የመድሃኒቴን ስም ስጠራ መደንገጥ ልማድ አድርጐታል ዲያቢሎስ መፈርጠጥ አዝ:- በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (2x) ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (3x) ባለዉለታዬ ይባረክ ጌታዬ (3x)