Song Lyrics

ሰው ታደርጋለህ

Caleb Tesfaye
Tegelbitoal Tarik
አዝ:- ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x) እንደ እኔ አይነቱን ክፉ ሰው ከኃጢአተኞች ሁሉ የባሰው እንዴት አሰብከኝ መረጥከኝ ምኔን አይተህ ነው የወደድከኝ የፍቅርህን ልክ ለመግለጽ ጌታዬ ቋንቋ የለኝም ከስግደት ከአምልኮ ሌላ የምሰጥህ እኔ ሌላ አላገኝም አዝ:- ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x) እናት አባት ሆነኀኛል እውነተኛ ወላጅ ሆንከኝ እያበላህ እያጠጣህ በእቅፍህ ላይ አሳደከኝ ውለታህ ዝም አያሰኝም የደስታ እምባ ያመጣል ያ ብዙ ቸርነትህ ቢወራ መቼ ያልቃል አዝ:- ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x) እኔን ከድጥ ላይ ለማንሳት ከማንም ጋር አልተማከርክ ልጄ ነው ወልጄሃለሁ ለማለትም በእኔ አላፈርክ በድኔን አፈር ልታለብስ ኑሮዬ እንዲሆን ምድር ሥር ትንሳኤ ልትሰጠኝ እንጂ አልመጣህ እኔን ልትቀብር አዝ:- ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x) ያለ መታሰቢያ እንዳልቀር ሲኦል እንዳልወረወር የሰይጣን መጫወቻ እንዳልሆን እንዳልፈጅብህ በእቶን በሕይወት መዝገብ ላይ ስሜን በከበረው ደምህ ጻፍከው አቤት የተረሳውን ሰው ደግመህ ወልደህ ሰው አደረከው አዝ:- ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ (ጌታ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x) ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ) ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection