ስለ ድሆች መከራ ስለ ችግረኞችም ጩኀት እግዚአብሔር አሁን እነሳለሁ ይላል መድሃኒት አደርጋለሁ በላይ በላይ እገልጣለሁ አዝ:- ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ የበረታውን ክንዴን ያያሉ በብዙ ብዙ ይባረካሉ (2x) ተስፋ የሚያደርጉት የሚረዳቸው ከእኔ በስተቀር ማንም የላቸው . (1) . ተሞልተው ጠርተዉኛል ቶሎ ድረስልን ብለውኛል ያለቀሱትን ለቅሶ አይቻለሁ ጸሎታቸውን ሰምቼዋለሁ ከእንግዲህ ላይራቡ ልጆቼ ጥላ ባመጡላቸው እጆቼ አዝ:- ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ የበረታውን ክንዴን ያያሉ በብዙ ብዙ ይባረካሉ (2x) መከራው በዝቶ ብዙ ተማረው ያለ ልክ አጥተው ተቸግረው ሞትን ሲመርጡ ከመኖር ይልቅ ያላቸው ሁሉ ተሟጦ ሲያልቅ በከንቱ ሲጨነቁ አየኋቸው እኔን የሚያክል ጌታ እያላቸው ስቃያቸውን አንጀቴ አልቻለም በቃ ብያለሁ ከእንግዲህ ሃዘን የለም አዝ:- ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ የበረታውን ክንዴን ያያሉ በብዙ ብዙ ይባረካሉ (2x) ሁሉ እቋቸው ብቸኛ ሆነው የሚደርስልን ኧረ ማነው ወዳች ዘመዶቻቸው ሸሿቸው አናውቃችሁም ብለው ካዷቸው ያጥላሏቸውን አሳፍራለው እንደተናቁ መች አስቀራለው ወዮ ባሉበት አንደበታቸው ሰው ሁሉ ያያል ሳዘምራቸው አዝ:- ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ የበረታውን ክንዴን ያያሉ በብዙ ብዙ ይባረካሉ (2x) እንጀራ ለአጡ መጋቢያቸው ነኝ ለተጠሙ ሁሉ የሚጠታ አለኝ ወዴኔ መጥተው ከቶ አያፍሩም የለመኑኝን አንዳች አያጡም ለጠሩኝ ሁሉ ባለጠጋ ነኝ የምስኪኖችን እምባ አባሽ ነኝ ሁሉን ሸለቆን መሙላት አውቃለሁ ችግረኞችን እባርካለው አዝ:- ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ የበረታውን ክንዴን ያያሉ በብዙ ብዙ ይባረካሉ (2x)