አዝ፦ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ሆ አማረኝ የአንተ መሆኔ ኢየሱስ ኩራት ኩራት አለኝ (2x) የበደሌን ብዛት አይተህ አልሄድክም ፊትህን አዙረህ ይቅርታህ ለእኔም ደርሶኛል . (1) . አስጀምረኸኛል እራራህልኝ ጌታዬ ለድካሜ ማረፊያዬ ለርሃቤ ነህ ጥጋቤ ለጥማቴ እርካታዬ አዝ፦ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ሆ አማረኝ የአንተ መሆኔ ኢየሱስ ኩራት ኩራት አለኝ ሌት ተቀን ሥምህን ስጠራ ድንቃ ድንቅህን ሳወራ የሰራህልኝን ተዓምር ውለታህን ስመሰክር ቢመሽ ቢነጋ አልሰለችም ክብሬ ነህ አላፍርብህም ቆርሼ መብላት የቻልኩት በአንተ ነው እንጀራ ያገኘሁት አዝ፦ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ሆ አማረኝ የአንተ መሆኔ ኢየሱስ ኩራት ኩራት አለኝ ግራ ቀኙን እየማተርኩ የሚረዳኝ እየፈለኩ አንተን አገኘሁ መልካሙን የሚባርክ ምስኪኑን ወጣሁኝ ከምድረበዳ ለምለም ደረቁ ጓዳ ቀና ሆነልኝ መንገዱ በቃ ለኑሮ መሰደዱ አዝ፦ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ሆ አማረኝ የአንተ መሆኔ ኢየሱስ ኩራት ኩራት አለኝ እኔን ደካማውን መርጠህ ብልሹነቴን ለውጠህ ውዳቂ የተጣልኩትን ሰው ይገርማል እንዴት ወደድከው ይብዛልህ ይኸው ምሥጋናዬ ዝማሬ ሆታ ዕልልታዬ በብዙ እረፍት ያሳረፍከው ኧረ እንደ እኔ የኮራ ማነው አዝ፦ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ሆ አማረኝ የአንተ መሆኔ ኢየሱስ ኩራት ኩራት አለኝ (2x)