አዝ፦ ገና ብዙ (3x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x) መድኃኒት አለ እናንተ ጋር አድኖ ፈውሶ የሚያስቀር መንገዱን ባካችሁ አሳዩን ወደ ሕይወት መግቢያውን በር ይሉናል ይለምኑናል የሚያቁን የምናውቃቸው ተፀይፈው ያባረሩን ከሰፈር ከመንደራቸው አዝ፦ ገና ብዙ (3x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x) የኃጥያት የችግር ቀንበር ተጭኖ በሰው ሁሉ ላይ መታወቂያችን ርሃብ ሆነ ተንቀናል ዞሮ እኛን ላይ የድሆችን ጩኸት ሰምቶ ከሰማይ ትዕዛዝ ያወጣል ቸነፈር ጉስቁልናውን አባሮት ጥጋብ ይጠራል አዝ፦ ገና ብዙ (3x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x) ከኃጥያት ጋር ጨዋታ ይዘው በጊዜያዊ ደስታ ታለው ክብራቸውን በነውር ሸጠው ፈጣሪያቸውን እረስተው ገለባ የሚበላ እሳት የመለኮት ኃይል ይመጣል አስመሳይ አታላይ ሁሉ ለአንዱ ጌታ ክብር ይሰጣል አዝ፦ ገና ብዙ (3x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x) ፅድቁ ሊገለጥ ማዳኑ ቀረበ ከትላንት ዛሬ የሆታ ቀን ሊመጣ ነው በምድራችን ላይ ዝማሬ በሥሙ ድንቅና ተዓምር ይሰራል ዝናው ይወጣል በቤት ጓዳ በአደባባይ ኢየሱስ አዳኝ ነው ይባላል አዝ፦ ገና ብዙ (3x) ክብር እናያለን ቀኑ ደርሷል የነገው ዶፍ ዝናብ ምልክቱ ተሸፍኖ ይሰማናል ወንጌሉ ጉልበት ኃይል አለው አይፈራም የትም ይገባል ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x) ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነውና ያሸንፋል (2x)