Song Lyrics

ፀጋ እፈልጋለሁ

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (2x) ጉልበቴ ሳይላላ ሳይቀንስ ትጋቴ በቤትህ መኖር ነው ሌት ተቀን መሻቴ ልገስግስ ወደፊት እየታደሰ ኃይሌ በመክሊቴ ላትርፍ ይብዛ ማገልገሌ አዝ፦ አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (2x) የድል አድራጊ ልጅ ባለ ድል አርገኸኝ ሽንፈታም ነኝ እያልኩ ሳወራ እንዳልገኝ የሰራህልኝን መልካሙን ሥራህን እንዳልረሳው እርዳኝ ያንን ውለታህን አዝ፦ አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (2x) ፍጻሜዬን አሳምር እንደ ጅማሬዬ በመልካም ይደምደም በፊትህ ሩጫዬ ሁሉ በአንተ ከአንተ ለአንተ ነውና ይኸው ክበርብኝ ዝቅ ልበልና አዝ፦ አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (2x) ለባዕድ አልሰጥም ይህን ጉብዝናዬን ወስኛለሁ አጽናው ቅዱሱን ምርጫዬን ልኑር እንደ ቃልህ ግራ ቀኙን ሳላይ እስካገኝ ርስቴን እስክገባ ሰማይ አዝ፦ አምላኬ አምላኬ ፀጋ እፈልጋለሁ ያለ አንተማ እርዳታ እንዴት እኖራለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection