አዝ፦ ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (2x) ስራብ እያበላኝ ስጠማ እያጠጣኝ ጉዴን ገመናዬን እየሸፈነልኝ ምን ጐደለህ እያለ ሌት ተቀን ያየኛል የድሃ አደግ አባት እግዚአብሔር ወዶኛል አዝ፦ ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (2x) ልቤን የጣልኩበት ተስፋ የማደርገው ጌታዬና አምላኬ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው ብድራት ፊቴ አለ የተዘጋጀልኝ ማንም አይወስደውም ኢየሱስ እያለልኝ አዝ፦ ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (2x) እንዳለፈ ውኃ ችግሬን አስረሳኝ የማይቻለውን አስችሎ አሳለፈኝ ሰላሙ በዛልኝ ሃዘኔ ተረስቷል በእግዚአብሔር በአምላኬ ደስታዬ ጨምሯል አዝ፦ ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (2x) ከማር ይልቅ ጣፍጦ አየሁት ኑሮዬን እጅግ አከበርኩት ቸሩ መድኃኒቴን በለመለመ መስክ ሁሌ ያሰማራኛል የበረከት አምላክ እግዚአብሔር ባርኮኛል አዝ፦ ከወደደ አይለቅም ይጣፍጣል ፍቅሩ ደስታ በደስታ ነው ከእርሱ ጋር መኖሩ (2x)