Song Lyrics

ሰው እንደጸና

Caleb Tesfaye
Motin Yereta Geta
አዝ፦ ሰው እንደፀና አይቆይ ሆኖ ገናና ጉልበቱ ይክደዋል ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (2x) አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (2x) ለውበትህ ወደር የለው (2x) በሰማይ በምድር መሳይ የለው (2x) ኃይሉ ከሁሉ የበረታ (2x) የጌቶች ሁሉ ነው ጌታ (2x) ለማንም አለ ሳይረታ (2x) አዝ፦ ሰው እንደፀና አይቆይ ሆኖ ገናና ጉልበቱ ይከብደዋል ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (2x) አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (2x) ብርቱ ኃያላኖች ተነሱ (2x) ሞት አይቀርምና ተረሱ (2x) እርጅና ድካም የማያውቀው (2x) ጥበብ ዕውቀቱ የጠለቀው (2x) ባለ ብዙ ክብር እግዚአብሔር ነው (2x) አዝ፦ ሰው እንደፀና አይቆይ ሆኖ ገናና ጉልበቱ ይከብደዋል ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (2x) አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (2x) የተነሱበትን ያዋርዳል (2x) ትዕቢተኞችን ይቀጣል (2x) የተፈሩትን የማይፈራ (2x) ዓይናቸው እያየ አለ እየሰራ (2x) እየናደ ግዙፉን ተራራ (2x) አዝ፦ ሰው እንደፀና አይቆይ ሆኖ ገናና ጉልበቱ ይከብደዋል ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (2x) አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (2x) ብቻውን ተዓምራት ያደርጋል (2x) ያለ ሠራዊት ይዋጋል (2x) በድል ላይ ድልን እያገኘ (2x) ጠላቶቹን አዋርዶ እየሸኘ (2x) አንድ እርሱ ብቻ ነው የተገኘ (2x) አዝ፦ ሰው እንደፀና አይቆይ ሆኖ ገናና ጉልበቱ ይከብደዋል ንብረት ሃብቱ ይሸሸዋል ይረሳል (2x) አምላኬ ግን እንዲህ አይደለም ጌታ ግን እንዲህ አይደለም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection