አዝ፦ በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (2x) ወጀቡን ተው አውሎ ነፋሱንም እየገሰጸ ረዳኝ አልተወኝም አሻገረኝ ወዲያ ወዲያ ማዶ አልመሸብኝ መጥቶልኛል ማልዶ አዝ፦ በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (2x) አብሮኝ ሲጓዝ ሜዳ ተራራውን መቼም ቢሆን አልረሳም ውለታዉን እያስቻለኝ ልቤን እያሰፋ ደጋገፈኝ ያዘኝ እንዳልጠፋ አዝ፦ በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (2x) አቤት ስንቱን ስንቱን አሳለፈኝ እየከለለ ክፉ እንዳያገኘኝ ጐኔ ባይቆም ለሁለ ባቄ ነኝ ማዕበሉ ወጀቡ በከደነኝ አዝ፦ በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (2x) አይዞህ ባዬ አጽናኜ ጌታዬ የሰላም ምንጭ ደስታዬ እርካታዬ ተወጣሁት ጉልበቴ ኃይል ሆኖ አላፈረም ማንም እርሱን ተማምኖ አዝ፦ በእሳት ውስጥ አልፌ አላቃጠለኝም በውኃ ውስጥ አልፌ አላሰጠመኝም የትናንቱ ኢየሱስ ዛሬም አልተወኝም እጁ እጄን ይዞታል አለቀቀኝም (2x)