Song Lyrics

አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን

Bruktawit & Getayawukal
Ye 11ngaw Seat Tselot Tiri
አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን በመድሃኒትህም ጐብኘን ህዝብህ ለአርባ አመታት ሲጓዝ ምድረ በዳ ሞገስ ስለሆንከው ከቶ ሳይጐዳ እያዘነብክለት ከሰማያት መና ስትጠብቅ ስትመራው በእሳት በደመና ሞገስህን አግኝቶ ህዝብህም በርትቶ ድል በድል አድርጓል ጠላቶቹን ረግጦ ህዝብህን ባሰብክበት ሞገስህ አስበን ማምለጥ እንድንችን ከከበበን ነገር አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x) ያየ የጋለው ፍቅርህ የቀድሞው ሕይወታችን ዛሬ ቀስሞብናል ቀዝቅዟል ልባችን አንድነት ሲጠፋ መለያየት በዝቶ ስም ብቻ ሆነናል ሕይወታችን ሞቶ ዛሬ ግን ጌታ ሆይ ጐብኘን በ??? ባሰብክበት ምህረት ልክ እንደህዝቦችህ እጆቿን ወደ አንተ ኢትዮጵያም ትዘርጋ ጊዜው አሁን ይሁን ሞገስህ ይብዛና አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x) በአንደበት ፍቅር የለበጥ አንድነት ቤትህን አረግነው ተንኮል የሞላበት በአፋችን ሌላ በልባችን ሌላ የያዝነውን እምነት አረግነው ደካማ መግባባት ይኑረን ቃላችን አንድ ይሁን እንደተናገርነው እንዲሁ እንድንኖር ዛሬ ለውጥን ስጠን ጌታ ለሁላችን በሞገስህ አስበን ይቀየር ልባችን አዝ፦ በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x) በህዝብህ ሞገስ አስበን (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection