Song Lyrics

እንዲህ አይነቷ ናት

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
ልባምን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል ከእግዚአብሔር ቃል ካልሆነ ከየት ይገኛል ከዝርግፍ ጌጥ ይልቅ ውስጧ የበለጠ በፀጋው መንፈሷ ሁሉ ያጌጠ ወርቅ አያምራት እርሷ ራሷ ወርቅ ናት ለይሉኝታ ምታስመጣው ጥሎሽ የላት መልካም አእምሮ የበሰለ ባህሪ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ፈሪ አዝ፦ እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት ከውጭ ውበት የውስጥ ውበቷ በልጧል አካሄዷ ንግግሯ ይገልጣል ማስተዋሏ ዕውቀቷ የበዛ ነው የማመዛዘን ችሎታ ሁሉ ያለው (በጣም) እንደ ሰነፍ ሴቶች አትናገርም በመከራም ውስጥ ተስፋን አትቆርጥም ከአጥንቱ ነው እርሷ የተሰራችው ለዚህ ነው ሁሉን ነገር የቻለችው አዝ፦ እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት የባሏም ልብ ይተማመንባታል እውነተኛው ፍቅር ይመግባታል ትገዛለች ለቃሉ ለሃሳቡ በግድ ሳይሆን አሸንፏት ፍቅሩ ተወስና እርሷ ለእርሱ ተሰጥታ በሌላ ወንድ ልቧም ሳያመነታ አንድ ለአንድ አይደለም የእርሷ ሂሳብ እንደቃሉ አንድ ናት ያለ ሃሳብ አዝ፦ እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት ገና ሌሊት በማለዳ ተነስታ (እንዲህ አይነቷ ናት) ምግብ ለቤቷ ሰዎች ሁሉ ሰርታ (እንዲህ አይነቷ ናት) ወገቧን በመቀነቷ ታጥቃለች (እንዲህ አይነቷ ናት) ስራዋን በጊዜው ትጨርሳለች (እንዲህ አይነቷ) እንድትለፋ አይደለም እርሱ ያገባት (እንዲህ አይነቷ) እረዳት ናት ሁሉም ነገር የገባት (እንዲህ አይነቷ ናት) ሰራተኛው አይደለችም ለቤቱ (እንዲህ አይነቷ ናት) ናት ለባሏ ድምቀቱ ውበቱ (እንዲህ አይነቷ) አዝ፦ እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት ውበት ሃሰት ነው ደምግባትም (ከንቱ ነው) ውበት ሃሰት ነው ደምግባትም (ከንቱ) እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (ትመሰገናለች) እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (እርሷ) (2x) እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (2x) አዝ፦ እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት እንዲህ አይነቷ ናት (4x) እውነተኛ ረዳት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection