Song Lyrics

ምክር

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
ከጉብዝናህ ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ አዎ ደስ ይበልህ ውደዳት አፍቅራት እርሷን እንደራስህ እህትህም ሚስትህም ባልንጀራህም ነች እረዳትህ ሆና ለአንተ የተሰጠች (2x) በረከት ካገኘ ሚስትን ያገኘ ሰው ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስ ከተሰጠ እያመሰገነ ስለዚህ ስጦታ ቤቱን በጽድቅ ይምራ ይንከባከባታል (2x) አዝ፦ የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (2x) እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (2x) አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንደተባለላት ለጌታ ለኢየሱስ እንደምትገዢ ለባልሽም ደግሞ እንዲሁ ተገዢ (2x) ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ እንደምትሆነው ክብሩ የት እንዳለ ቃሉ ካጸደቀው ማፈሪያህ እንዳይሆን አንቺም እንዲህ ሁኚ ግን ልባምነትን ከቃሉ አግኚ (2x) አዝ፦ የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (2x) እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (2x) የብልህ ቤት ይሁን ክርስቶስ ራስ ሆኖ ዐይንም በእርሱ አድርጐ በስሙ ተማምኖ መንገዱን ዝለቁት የኑሮን ጐዳና ግልጽ ሁኑ ሁሉን ነገር ተከባበሩና (2x) ዕውቀትን እንደዘውድ በላያቹህ ጫኑ ጥበብን እንዳትዉ ሞኞች እንዳትሆኑ በፍቅር ለጸና ለተቻቻለ ሰው ጋብቻ ክቡር ነው መኝታው ንጹህ ነው (2x) አዝ፦ የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (2x) እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (2x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x) እግዚአብሔር አለ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection