Song Lyrics

ሙሽሪት ሙሽራው

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
አዝ፦ ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ ኦ ስራው ግሩም ነው ደስ ብሎናል ዛሬ (አሜን) ልዑል አሰናዳ (አሜን) ባርኮት የሚበላ (አሜን) ከማመስገን ብቀር (አሜን) ምን ይባላል ሌላ (አሜን) የዘለዓለም አምላክ (አሜን) ወደ እረፍት አመጣን (አሜን) ከብቸኝነቱ (አሜን) መንደር እያወጣ አዝ፦ ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ ኦ ስራው ግሩም ነው ደስ ብሎናል ዛሬ (አሜን) አክሊል የለበሰ (አሜን) ሙሽራው ሲያምርበት (አሜን) በጌጥ ሽልማቷ (አሜን) ሙሽሪት ሲያምርባት (አሜን) ነገር ግን እግዚአብሔር (አሜን) ጽድቅን አቆናጽፎ (አሜን) ሰውን ለዚህ ያበቃል (አሜን) ሁሉን አሳልፎ አዝ፦ ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ ኦ ስራው ግሩም ነው ደስ ብሎናል ዛሬ አዲስ ጐጆ ወጪ በይ ባርኮቱን ጠጪ ብሎ የመረቃት ደጉ ቸሩ አባት እረድቷት አምላኳ ሲለወጥ ታሪኳ ጐጆን ማን አስወጣት ጌታ ነው ያገዛት (2x) ምህረቱ ብዙ ነው ምህረቱ የጌታ በእርሱ ተጀምሯል የሙሽሪት ቤቷ (4x) አዲስ ስፍራ ሰጥቶ በኑሮም ገብቶ ጌታ አደላደለው ተመስገን አስባለው ይህን ሁሉ ነገር ስላሳየን ይክበር ቃሉን ላላጠፈው ምሥጋናችን ይሄው (2x) ምህረቱ ብዙ ነው የእግዚአብሔር ምህረቱ በእርሱ ተጀምሯል የሙሽራው ቤቱ (4x) (አሜን) ፍቅር ግን እስከሞት (አሜን) ብርቱ ስለሆነ (አሜን) እርሷም ለእርሱ ሆነች (አሜን) እርሱም ለእርሷ ሆነ (አሜን) ጌታ ያነደደውን (አሜን) የፍቅርን እሳት (አሜን) ብዙ የጥፋት ውኃ (አሜን) አይችልም ሊያጠፋት አዝ፦ ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ ኦ ስራው ግሩም ነው ደስ ብሎናል ዛሬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection