Song Lyrics

አብሬ ጨምሬ

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
አዝ፦ እኔም ይህን ጌታ ላክብረው ላክብረው ከእነርሱ ጋር አብሬ አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ አብሬ ዕልልታን ጨምሬ አብሬ አምልኮን ጨምሬ አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (2x) አላማሩም ወይ ዛሬ አላማሩም ወይ (2x) እውነት የሆናቸው ጌታ አይደለም ወይ (2x) ሞገስ የሆናቸው ኢየሱስ አይደለም ወይ (2x) አላማሩም ወይ ዛሬ አላማሩም ወይ (2x) በስራና በቃል ብርቱ የሆነው ጌታ እጃቸውን ይዞ ሁሌ እያበረታ ለዚህ ላበቃቸው ስንቱን እየመታ እዚህ አደረሳቸው ክፉን እየመታ ቃል የገቡት ቤተሰቦቹ (3x) ከሁሉም ሚበልጥ አግኝቷል እጁ (3x) ቃል የገቧት ቤተሰቦቿ (3x) ወሰነች ልትኖር ከባሏ ብቻ (3x) ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ሁሉ በሰርጉ ያላችሁ ተጋባዥ በሙሉ ላጤነት አብቅቶ ብቸኝነታቹህ በቃ ለቀው ሄዱ ከቀድሞ ቀያቸው አመስግኑ (ኦሆ) አጨብጭቡ (አሃ) ለአምላካችሁ (ኦሆ) እልል በሉ (አሃ) (2x) አዝ፦ እኔም ይህን ጌታ ላክብረው/ላንግሰው ላክብረው/ላንግሰው ከእነርሱ ጋር አብሬ አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ አብሬ ዕልልታን ጨምሬ አብሬ አምልኮን ጨምሬ አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (2x) ከመጀመሪያው (3x) እግዚአብሔር አንድን ወንድ ለአንድ ሴት አድርጐ ሰራው (4x) ከመጀመሪያው (3x) እግዚአብሔር አንድን ሴት ለአንድ ወንድ አድርጐ ሰራት (4x) ይህ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬም ይህ ነው (4x) ይህ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬም ይህ ነው (4x) አላማሩም ወይ ዛሬ አላማሩም ወይ (2x) በስራና በቃል ብርቱ የሆነው ጌታ ሁሉን አሳመረ እጁ አለበት ይሄው አሳመረው ቃሉ አለበታ የቃል ኪዳን አምላክ ክንዱ አለበት አላማሩም ወይ ዛሬ አላማሩም ወይ (2x) እርሱ ያገናኘውን ሰው አይለየውማ ማጣመር ለሚችል ከፍ ይበል በዜማ ሰው ማድረግ ለሚችል ምሥጋናን ላሰማ መባረክ ለሚችል ዕልልታን ላሰማ ቃል የገቡት ቤተሰቦቹ (3x) ከሁሉም ሚበልጥ አግኝቷል እጁ (3x) ቃል የገቧት ቤተሰቦቿ (3x) ወሰነች ልትኖር ከባሏ ብቻ (3x) ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ሁሉ በሰርጉ ያላችሁ ተጋባዥ በሙሉ ላጤነት አብቅቶ ብቸኝነታቹህ በቃ ለቀው ሄዱ ከቀድሞ ቀያቸው አመስግኑ (ኦሆ) አጨብጭቡ (አሃ) ለአምላካችሁ (ኦሆ) እልል በሉ (አሃ) (2x) አዝ፦ እኔም ይህን ጌታ ላክብረው/ላንግሰው ላክብረው/ላንግሰው ከእነርሱ ጋር አብሬ አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ አብሬ ዕልልታን ጨምሬ አብሬ አምልኮን ጨምሬ አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection