ገዢና ተገዢ መኳንንት ሹማምንት የአገሬው ህዝብ ሁሉ የተሳተፉበት እምቢልታ መሰንቆ በገናና ዋሽንት ሁሉም ተሰለፎ ለአንድ ሰው ትዕቢት አቤት ትዕቢት (2x) የአንድ ንጉሥ ትዕቢት አገር ሲያሰግድ ህዝቡን ሲያንቀጠቅጥ ሶስት ደፋር ሰዎች ጣዖት ያለመዱ አንሰግድም ሲሉ በዓል አበላሹ ንጉሡም ሲሰማ በትዕቢት ተቆጣ እቶኑን ጨመረው እጥፍ እንዲነድ ሌላ ጉድ ፈላ አንሰግድም ያሉ በትዕቢት በጋለ እቶን ውስጥ ተጣሉ ወድቀው ተቃጥለው አረው ተኮማትረው መች ቀሩ መች ቀሩ ምንም ቢታሰሩ ተፈታ ገመዱ እያለ አዳኙ ጭራሽ ወዲህ ወዲያ ይራመዱ ጀመር የተስማማ እስኪመስል እንዴትስ አይመች እንዴትስ አይድላ ኢየሱስ ካለማ (2x) ትዕቢቱ ተመታ የንጉሡ ሲበለሻሽበት ድግሱ ሶስት ሰዎችን ጥሎ አራት ሲሆኑበት ነገር ግራ ሆነበት ንጉሱም እንዲህ አለ አዋጁን ቀየረ እየደነገጠ እነዚያን ብሩካን አውጧቸው ከእሳት እናምልከው በቃ የእነርሱን አምላክ (2x) ሁሉም ሰው ያምልከው ይስገድለት ፊቱ ያስደንቃልና የማዳን ጉልበቱ እንደፋ ፊቱ እስቲ ጐምበስ (2x) ይባልለት ይሰገድለት እስቲ ጐምበስ (2x) ይባልለት ይሰገድለት አያልቅበት (2x) ማዳኑ አያልቅበት አያልቅበት መታደጉ አያልቅበት አያልቅበት ምህረቱ አያልቅበት እስቲ ጐምበስ (2x) ይባልለት ይሰገድለት እስቲ ጐምበስ (2x) ይባልለት ይሰገድለት (2x)