ተስፋ ቆርጬ ወደኋላዬ አልልም በጥቂቱ ዝዬ አልመለስም ብትገድለኝም ብታድነኝም ብትሰጠኝም ብትነሳኝም እጅህን እጠብቃለሁ ከፊትህ አልሄድም አንተን የለመነህ በፊትህ ጠብቆ ሁሉን እንደምትችል እንደምትሰጥ አውቆ ጊዜውን ብታረዝምም እምነቱን ልትፈትን እርሱን የጠበቀው መች አጣው ባርኮቱን አግኝቷል ከጌታ አጽንቶ እምነቱን እኔም መስቀልህ ስር ሆኜ እጠብቃለሁ ምን እንደምትሰራ እጅህን አያለሁ ጉልበቴን በፊትህ አምበረክካለሁ ቃሌንም በቤትህ ዝም አሰኘዋለሁ አንተ ምትሰራውን በሙሉ አያለሁ አንዲት ከነአናዊት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ልጄ በእርኩስ መንፈስ ተይዛ ትስቃያለችና እባክህ እራራልኝ ; እያለች ጮኸች እርሱ ግን አንድም ቃል ሳይመልስላት ዝም አለ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረብ ብለው ይሂች ሴት እየተከተለችን ስለምትጮህ እባክህ አሰናብታት ሲሉ ለመኑት እርሱም እኔ የተላኩት ከእስራኤል ቤት እንደበጐች ለጠፉት ብቻ ነው ሲል መለሰ። ሴትዬዋ ግን ቀርባ በእግሩ ስር ተንበረከከችና ጌታ ሆይ እባክህ እርዳኝ አለችው። ኢየሱስም የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መጣል የተገባ አይደለም አለ። እርሷም ጌታ ሆይ እርግጥ ነው። ነገር ግን ውሾችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዐድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ አንቺ ሴት እምነትች ትልቅ ነው። ስለዚህ እንደፍላጐትሽ ይሁንልሽ አላት። የሴትየዋም ልጅ በዚያን ሰዓት ዳነች። በለእርሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል ከጌታው ሚጠብቅ እርሱ ደግሞ ይከብራል እኔም ከአንተ ብቻ እጠብቃለሁኝ የአማረውን ፍሬ ለመብላት ጓጓሁኝ አይቀርም አንድ ቀን ደግሞ እከብራለሁኝ ብትሰጠኝም ብትነሳኝም እጅህን እጠብቃለሁ ከፊትህ አልሄድም ቃሌንም በቤትህ ዝም አሰኘዋለሁ አንተ ምትሰራውን በሙሉ አያለሁ