በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ ስለ እራሴ ስለ ግሌ ስለ ቤቴ ስለ አገሬ ስለ ኑሮ ስለ ሕይወት ስለ ያዝኩት አገልግሎት የማዋይህ አለኝና ልምበርከክ ፊትህ እንደገና የማዋይህ አለኝና ልምበርከክ ፊትህ እንደገና (2x) የእግዚአብሔር በግ የሆንከው ልቤን በፍቅርህ ያደስከው ጓዴ/ጌታ ኢየሱስ እስቲ ና የማዋይህ አለኝና (2x) ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ አንድ ሰው እስኪነጋ ድረስ ይታገለው ነበር እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሽሉዳ??? ነካው ያዕቆብም የጭኑን ??? ሲታገለው ደነዘዘ እንዲህም አለው ሊነጋ አቅላልቷልና ልቀቀኝ እርሱም ካልባረከኝ አለቅህም አለው እንዲህም አለው ስምህ ማነው? እርሱም ያዕቆብ ነኝ አለው ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባላል እንጂ ያዕቆብ አይባልም በዚያም ስፍራ ባረከው። በረከትህን ልጥራ በእኔ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በቤቴ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በአገሬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ቤተሰቤን ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ስራዬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ትምህርቴ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ ትዳሬ ላይ በዚህ ማለዳ በረከትህን ልጥራ በእኔነቴ በዚህ ማለዳ ካልባረከኝ አለቅህም (4x) ካልዳሰስከኝ አለቅህም (2x) ካልፈወስከኝ አለቅህም (2x) ካለወጥከኝ አለቅህም (2x) ካላደስከኝ አለቅህም (2x) ካልባረከኝ አለቅህም (2x)