ሊነጋጋ ሲል ኢየሱስ በማለዳ ተነስቶ ወጣ ለመጸለይም ወደ አንድ ገለልተኛ ቦታ ሄደ ሌሊቱ ሲነጋ ጐህ ሲቀድ አእዋፍ ሲንጫጩ በአንድነት በዜማ ፈጣሪን ለማምለክ ሲወጡ ሁሉም ከያሉበት እኔ ግን መኝታዬ ሞቀኝ ዝምብለሽ ተኚ ተኚ ቢለኝ መኝታዬን ወዲያ ገፍፌ ለጸሎት ነቃሁኝ ከእንቅልፌ ለጸሎት መንፈሴ ሲነቃ ሥጋዬ ባይደሰት ቢከፋ ሳይወድ በግዱ ያብርና መጸለዬ ይቀጥላል ገና ስሙን ስጠራው የጌታዬን ያድሰዋል ደካማው ጐኔን ቅባቱ መፍሰስ ይጀምራል ለጸሎት ጉልበቴን ያድሳል አዝ፦ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ ድልን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መልስን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ እንደሚሰማ አምናለሁ አንዳንዴ ውስጤ ጸልይ ሲለኝ ስጋዬ ግን ሲያታልለኝ ቆይ ትጸልያለህ በኋላ እያለ ጊዜዬን ሊበላ ግን ዳንኤልን ጉድጓድ ያስጣለው አትጸልይ የሚል ህግ ነው ቢያስመርጡት ከምንም ነገር ጸሎት ነው ለእርሱ ትልቅ ነገር ይህንን ሳስታውስ እነቃለሁ ስጋዬን ተወኝ እለዋለሁ ስታዘዝ ለነቃው መንፈሴ ለጸሎት ተጋልኝ ጉልበቴ ጸሎት ትልቅ መሳሪያዬ ነው ሰይጣንም ይሄ ስለገባው እንዳልጸልይ ቢታገለኝም ምክኒያትን ለሥጋዬ አልሰጥም አዝ፦ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ ድልን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መልስን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ እንደሚሰማ አምናለሁ አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላልው አባትህ ጸልይ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል ግራ ሲገባኝ በሕይወቴ መምበርከክ ሲያቅተው ጉልበቴ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ስሞላ መፍትሄ መልስን ሳጣ መላ ከመጸለይ ይልቅ በፊቱ ሳወራ ላገኘሁት ሁሉ ይባባስብኛል ችግሬ ያጐብጠኛል ያ ጠብቆ ቀምበሬ ግን በሬን ዘግቼ ስገባ የውስጤን ሁሉ ወደ ሚረዳ በጸሎት ዙፋኑ ስር ስወድቅ ይታደሳል ውስጤ በድንገት ያልወጣሁት ችግር ጸልዬ ፍፁም የለምና በሕይወቴ ባልጸልይ እራሴን እጐዳለሁ ይህንን በተግባር አውቃለሁ አዝ፦ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ ድልን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ መልስን አግኝቻለሁ እጸልያለሁ (3x) በፊቱ ወድቄ ለምኜ እንደሚሰማ አምናለሁ