ጌታ ለሕይወቴ አንተ መሪ ሁነህ ለኑሮዬም ጥላ ሃሩር እንዳይጐዳኝ እባክህ ሁንልኝ እኔ ደካማ ነኝ አንተ ግን ብርቱ ነህ ጸንተህ የምትገኝ ጌታ ሆይ ለልጅህ የምታውቅ አንተ ነህ የሚበጀኝንም ሁሉን አዘጋጅተህ ለእኔ ታስባለህ ትጠነቀቃለህ የማይጠቅመኝንም ወዲያ ትጥላለህ የልቤ ጓደኛ በአንተ እረካለሁ የምትሰጠኝንም እቀበልሃለሁ ሁሉን እንደወደድህ እንደ ፈቃድህ እንግዲህ አድርገው ደስ እንዳሰኘህ ከእንግዲህስ እኔ ምንም አልናገር ሰጥቼዋለሁኝ ሁሉን ለእግዚአብሔር በደስታም በሃዘን ተመስገን እያልሁኝ እርሱም ሚያደርገውን እኔ አያለሁኝ አሜን አሜን አሜን