እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምጹን ይሰጣል ሰራዊቱም ይህን ይመስላል መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው የማንኮራፋቱ ክብር የሚያስፈራ ነው በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል በፍርሃት ላይ ይስቃል አይደነግጥም ከሰይፍ ፊቱን አይመልስም የመለከትን ድምጽ ሲሰማ እሰይ ይላል ገለባውንም እንደሚባላ እንደ እሳት ድምጽ ለሰልፍም እንደተዘጋጀ ለብርቱ ሕዝብ ያኮበኩባል እንደ ኃያላን ይሮጣሉ ከሰልፈኞችም በቅጥር ይወጣሉ እንደ ሌባም በመስኮት ይገባሉ እያንዳንዱ በመንገዱ ይራመዳል የራሱን መንገድ ይጠበጥባል ። ከእነርሱ የሚያመልጥ የለም ። ምድሪቱም ከፊታቸው የተነሳ ትናወጣለች ። እነሆ እንዲህ ያለ ሠራዊት በምድረ ኢትዮጵያ ይገለጣል አሜን! ሃሌሉያ! አዝ፦ ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) መልኩ የፈረስ ሩጫው የፈረስ አንዴ ከገባ የማይመለስ ዓይኑ የፈረስ ድፍረት የፈረስ አንዴ ከመጣ የማይመለስ አዝ፦ ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) አንገቱ ጋማ እንደለበሰ እየጋለበ እየገሰገሰ ዘው ብሎ ገባ ጦር ሜደ መሃል ፈረሱ እንደሆን ሰልፍን ይወዳል ከት ብሎ ይስቃል በፍርሃት ላይ አይመለሥም ጦርነት ሳያይ እርሱ ግድ የለው ጭራሽ ይሮጣል አይደነግጥ ኧረ እሰይ ይላል ጦርነት ሽቶት ደስታ የሚሞላ ከፈረስ በቀር ማን አለ ሌላ ልክ እንደ ፈረስ የሚያስፈራ ሰራዊት መጥቷል ኃይል የተሞላ ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ኃያላን መጡባት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ኃያላን መጡላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ጌታ ደረሰላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኮበኩባል በሩን ብትዘጉ በመስኮት ይገባል አንዱ ካንዱ ጋር ሳይገፋፋ አንዱ በሌላው ሳይገፋፋ መንገዱን ይዞ ቀጥ ብሎ ይሄዳል በራሱ መንገድ ይጠበጥባል በሰልፍ መሃከል በፍልሚያው ስፍራ የራሱን ወገን ስለሚያጣራ ተሳስቶ ረስቶ በወንድሙ ላይ አይለውጠውም ለይቶ ሳያይ ስለዚህ መቁሰል መሰነከካከል በፍፁም የለም በእርሱ መሃከል ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ኢየሱስ መጣላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ምህረት ወረደላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) ይሄ ሰራዊት በሰልፍ ሲያልፍባት ዘንድሮስ ጉድ ነው ምድር ፈርዶባት ትናወጣለች ይህንን አይታ በተራራው ላይ ኮቴውን ሰምታ በእቅጥቃጤ ያናውጧቷል እንቆቅልሿን ይፈቱላታል እስራቷንም የሚበጣጥስ ሰራዊት መጥቷል የሚገሰግስ ባታምነው እንኪ አንተም እኮ አለህ የዚህ ሰራዊት ዋነኛ አባል ነህ አታውቂም እንጂ አንቺም እኮ አለሽ የዚህ ሰራዊት ዋነኛ አባል ነሽ ምድር ጉድ ፈላባት (2x) እኛ መጣንባት ምድር አለፈላት (2x) እኛ መጣላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ሰራዊት በዛላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) እኔ መጣሁላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) እጁን ሲጭን ደዌ ይፈወሳል በስብከታቸው ሰው ይመለሳል በትምህርታቸው የስህተት ትምህርት ሊነቀል ??? ከስር ከመሰረት ዝማሬንማ ከጀማመሩ መናፍስቶችን ያራውጣሉ ጌታ መድሃኒት ስላደረጋቸው ለምድሪቱ ፈውስ መፍትሄ አላቸው ተረኛ አድርጐ ስለላካቸው ለሰራተኞች ልቀቁላቸው እኛ እንቢ ብንል ሊሆን ግድ ነው የሰራዊቱ መሪ እግዚአብሔር ነው ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር አለፈላት (2x) ኃይለኞች መጡላት ምድሬ አለፈላት (2x) ጌታዬ ጐበኛት ምድሬ አለፈላት (2x) ሰራዊት መጣላት ምን ዓይነት ሰራዊት ነው የመጣው ምን ዓይነት ሰራዊት ነው (2x) አላማቸውን ለገንዘብ ሲሉ ለጥቅማጥቅም የማይደለሉ ለያዙት እውነት ቆራጦች ናቸው በፍፁም የለም የሚያስፈራቸው ውስጣቸው በቃል ስለተሞሉ ስራ እያላቸው ቁጭ የማይሉ ቀልድና ተረት የማያወሩ የሚሯሯጡ ወደ መከሩ እነዚህ ናቸው ሰራተኞቹ ለእግዚአብሔር ስራ ልብ አድርሶቹ እነኛዎቹም አበቃላቸው ሰራዊቶቹን ጌታ አስነሳቸው ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ቆራጦች መጡባት ምድር አለፈላት (2x) ጌታ ሰው ላከላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) መፍትሄ ተገኘላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ኃይለኞች መጡላት ማነው የሰራዊቱ አለቃ ማነው የሰራዊቱ (2x) የሰራዊቱ ዋና አለቃ ጌታ እግዚአብሔር ትዕዛዝ አወጣ ከፈተላቸው የምድሪቱን በር ያለውን እርግማን እስኪሰባበር እነርሱም ቆራጥ ወሳኞች ናቸው የተሰማሩ በየድርሻቸው ውስጣቸው ፀጋ ስለተሞሉ ሲጠባበቁ እስካሁን አሉ ከእግዚአብሔር አብ እንኳን ቃል ወጥቶ ተቁነጥኗል ውስጣቸው ሞልቶ የልቡን ሃሳብ ሊፈጽሙ ነው ዞር በሉላቸው ጊዜው የእነርሱ ነው ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ሰራዊት መጣባት ምድር ጉድ ፈላባት (2x) ወሳኞች መጡባት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ልፍስፍስ ጠፋላት ኢትዮጵያ አለፈላት (2x) ወሳኞች መጡላት