ለሥጋዊ ነገር እራስን ማስለመድ ከእግዚአብሔር ሀሳብ እርቆ መራመድ ለጊዜያዊ ደስታ ነፍስን አስገዝቶ ዛሬን ብቻ መኖር የነገውን ትቶ አይጠቅመኝም ከቶ ይህን አውቄዋለሁ እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው በሰው ወግ ተይዞ በይሉኝታ እስራት ዛሬን ላያሻግር ለእንጀራ መገዛት እውነትን ከመግለጥ በውሸት ከልሎ መምሰል የሌለበት የማስመሰል ኑሮ አይጠቅመኝም ከቶ ይህን አውቄዋለሁ እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው ታላቅና ክቡር ሕይወትም የሆነ ከአማራጮች ሁሉ እጅግ የተሻለ አሁን ላለውና ለመጪው ዘመኔ እግዚአብሔርን መምሰል ያዋጣኛል ለእኔ ያዋጣኛል አዎ ይህን አውቄያለሁ እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሪያለሁ ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው ከኋላ ያለውን በሙሉ ረስቼ የፊቴን ለመያዝ እጆቼን ዘርግቼ ምልክት አይቼ መፍጠን ጀምሬያለሁ መጠራቴ ዋጋው ጌታዬን መምሰል ነው ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው ስለዚህ የሚይዘኝ የሚያስቀረኝ ማነው ሁሉንም እየጣስኩ ወደፊት ሄዳለሁ