Song Lyrics

አስደስተዋለሁ

ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው በአለት ነው በአሸዋ ቤትህ በምን ላይ ነው (2x) ቤቴ አሸዋ ላይ ነው የተመሠረተው እስከአሁን ሰላም ነው ችግርም አላየሁ በጋው ተስማምቶኛል ምን ችግር ይመጣል ውኃ እኮ በአሸዋ ወዲያው ይመጠጣል መስሎሃል ይልቅ ወጪ አታውጡ አለት አትቧጥጡ ወጪን ይቀንሳል አሸዋ እኮ ሞልቷል የእኔስ ቤት አምራለች በጣም ዘንጣለች ላለሁበት ጊዜ ተመችታኛለች ተው ይቅርብህ አሸዋ ከሆነ የቤትህ መሠረት (2x) አቤት ጉድ ፈላበት አሸዋ ከሆነ የቤትህ መሠረት (2x) አቤት ጉድ ፈላበት ክረምት የመጣ ቀን ዝናብ የመጣ ቀን ጐርፉ የመጣ ቀን ንፋስ የመጣ ቀን ጠራርጐ ይወስደዋል አንዱንም ሳያስቀር ገንዘብህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት ዕውቀትህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት አቤት ጉድ ፈላበት ሥልጣንህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት ጥበብህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት አቤት ጉድ ፈላበት ችግር የመጣ ቀን ሃዘን የመጣ ቀን መከራ የመጣ ቀን ማጣት የመጣ ቀን ጠራርጐ ይወስደዋል አንዱንም ሳያስቀር ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው ባለት ነው በአሸዋ ቤትህ በምን ላይ ነው (2x) ቤቴ በዓለት ላይ ነው የተመሠረተው ችግሩም በሽበሽ ነው መከራብ ብዙ ነው ጐርፉ ሲወርድብኝ ነፋስ ሲነፍስብኝ አለት ላይ ስላለሁ ቤቴ አልፈረሰብኝ ኧረ ምንም አትሆን አለት በቀላሉ አይገኝም ሲሉ የምደክም መስሎኝ ድሮ ተሞኘሁኝ የአሸዋ ነጋዴው ነበርና ወሬው ቤቴን በዓለት ብቻ ሰራሁ ከነአካቴው ደግ አድርገሃል አለቱ ከሆነ የቤትህ መሠረት አለቱ ከሆነ የቤትህ መሠረት በቃ አለፈለት (2x) ክረምቱ ቢመጣ ዝናቡም ቢወርድ ጐርፉ ቢንደረደር ንፋሱም ቢነፍስ የአንተ ቤት እንደሆን ፈጽሞ አይላወስ ኢየሱስ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት ቃሉ ከሆነልህ የሕይወትህ መሠረት በቃ አለፈለት (2x) መከራ ቢመጣ ችግር ቢደርስብህ ሃዘን ቢያጋጥምህ ማጣት ቢያስቸግርህ አትነቃነቅም አለት ላይ ስላለህ አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x) አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x) ያየሁት በስራ ዓይን አይደለም ግን እርግጠኛ ነኝ በሕይወቴ አይቼዋለሁ ፍቅሩ ሲዳስሰኝ (4x) አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x) አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x) ያየሁት በስራ ዓይን አይደለም ግን እርግጠኛ ነኝ በሕይወቴ አይቼዋለሁ ፍቅሩ ሲዳስሰኝ (4x) አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x) አለቱ ነው መሠረቴ (4x) ኢየሱስ ነው መሠረቴ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection