Song Lyrics

ሥራህን ትፈፅማለህ

አዝ፦ በዘመን በዓመታት መሃል ሥራህን ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ማነው ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (2x) ባለፈው ዘመን የሰራ ዛሬም ክንዱ ያልደከመ መንግሥቱን በደንብ አስፋፋ እኛም ደግሞ የቀጠለ ኃይል ብርታት ጉልበት ሆኖልን የምንሰራው አብረን ነው አሁን ካሳየን ይበልጣል ነገን በእኛ የሚገልጠው ሰራተኛ አድርጐናል ለቤቱ መስራት ያላቆመ ከጥንቱ በሚሰራበት ቀን በቤቱ መጠቀሚያው ነን እኛ ገንዘቡ (2x) አዝ፦ በዘመን በዓመታት መሃል ሥራህን ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ማነው ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (2x) በአሁኑ ዓመት እንዳየነው በሚመጣው ዓመት አይሆንም ብሶበት እንጂ ቀንሶ ሥራው አይከናወንም እጥፍ ድርብ እየሆነ ፍሬው ገና ይበዛልናል በክልል አይወሰንም የምድርን ፊት ይሸፍናል የምሩን ይነሳል ንጉሡ እናንተ አገልጋዮች ተነሱ ገና ብዙ ጉድ ነው የሚታየው እግዚአብሔር ሀሳቡ እኛ ላይ ነው (2x) አዝ፦ በዘመን በዓመታት መሃል ሥራህን ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ማነው ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (2x) ዛሬ ከተገለጠልን የነገው ደግሞ ይብሳል የሚመጣልን ዝማሬ የዛሬን ሁሉ ያስረሳል ማሽቆልቆል ወደታች መውረድ መቀነስ መዳከም መዛል ከዚህ በኋላ በእኛ ላይ በኢየሱስ ሥም አይሰራም ተሻገር የሚል ወደ ማዶ ሰምተናል ድምፅ ከሰማይ ወርዶ ተሻግረን ደግሞ እንሄዳለን የነገውን ዘመን እናያለን (2x) አዝ፦ በዘመን በዓመታት መሃል ሥራህን ትፈፅማለህ የሚከለክልህ ማነው ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection