Song Lyrics

አትገመትም

አዝ፦ አተገመትም በእኔ ቃላት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺህ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (2x) የችግር ቋጠሮ ውስብስብ ሲልብህ መግቢያ መውጫ ጠፍቶህ ግራ ሲያጋባህ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ደግሞ ሲፈታታ ችግር ሁሉ ሲተን የትላንት ጨለማ እንደጉም ሲበተን አንተ ከሁሉ በላይ ነህ አዝ፦ አተገመትም በእኔ ቃላት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺህ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (2x) አንተን እንዳላመልክ ከፍታው ዝቅታ ከቶ አያግደኝም አይጠፋኝ ዕልልታ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ውስጤ ቅኔ ሞልቷል ከገጠመኝ በላይ አምላኬ እግዚአብሔር ነህና ኤልሻዳይ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ አዝ፦ አተገመትም በእኔ ቃላት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺህ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (2x) ሁሉም ነገር ጠፍቶ በቤቴ የሚበላ ያልጠበኩት ነገር ሲሆንብኝ ሌላ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ ደግሞ በጐጆዬ በረከት ሲሞላ ሁሉም ነገር ሞልቶ ሲተርፈኝ ለሌላ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ አዝ፦ አተገመትም በእኔ ቃላት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺህ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (2x) ሲሞላ ዘምሬ ሲጐድል ላላለቅስ በምንም ሁኔታ አምልኮ አልቀንስም አንተ ከሁሉም በላይ ነህ እታመንሃለሁ በምሥጋና ሆኜ ድል እንደምትሰጠኝ በስምህ አምኜ አንተ ከሁሉም በላይ ነህ አዝ፦ አተገመትም በእኔ ቃላት ብዛት አትወሰንም በአእምሮ ስፋት አትገመትም በሺህ ቃላት ብዛት አትወሰንም በጠቢባን ጥበብ አንተ ከሁሉ በላይ ነህ በላይ ነህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection