Song Lyrics

ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ

Bruktawit & Getayawukal
Hitsanat Wede Ene Yimtu
ሚጡ ሚጡ ነይና አባባ እንቅልፋቸው ሳይመጣ ምከሩን እንበላቸው እንደትላንትና ። ውይ እኔ እኮ በጣም ነው ምወደው የሳቸውን ምክር ። እሺ ነይ ደስ ይለኛል አባባ አባባ? ምክር ምከሩን አባባ ። ምክር አላችሁ? አዎ አዎ ። እሺ እስቲ ዛሬ እስኪ ደግሞ ከምሳሌ መጽሃፍ እስቲ አንድ ምክር ልምከራቹህ ። አሺ እሺ ። እንደዚህ ይላል ልጆቼ ። ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ ትዕዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ ትዕዛዜንም ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ ያላል ። የእግዚአብሔርን ቃል ስትጠብቁ በሕይወት ትኖራላችሁ እሺ? እሺ! ጐበዝ ልጆች ። እስቲ እቼን መዝሙር ደስ እያላችሁ ዘምሯት ። እሺ አባባ ሚጡ ነይ! ጥበብ ማስተዋል ስጠኝ እያላችሁ አምላክን ለምኑት ። ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቅ ትዕዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ ትዕዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ ህጌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ በጣቶችህ ተሰራቸው በልብህ ጽላትም ጻፋቸው ጥበብን አንቺ እህቴ ነሽ በላት ማስተዋልንም ወዳጄ ብለህ ጥራት ልጄ ሆይ ቃሌን ጠብቂ ትዕዛዜንም በአንቺ ዘንድ ሸሽጊ ትዕዛዜን ጠብቂ በሕይወትም ትኖሪያለሽ ህጌንም እንደ ዐይንሽ ብሌን ጠብቂ በጣቶችሽ ተሰራያቸው በልብሽ ጽላትም ጻፊያቸው ጥበብን አንቺ እህቴ ነሽ በያት ማስተዋልንም ወዳጄ ብለሽ ጥራያት ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ ጌታ ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ (ለእኔ) ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ ጌታ ጥበብ ማስተዋል ዕውቀትን ስጠኝ (ለእኔ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection