Song Lyrics

የሙሽራው የሙሽሪት

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
አዝ፦ የወንድ ሙሸራ ድምጽ የሴት ሙሸራ ድምጽ ቸር ነውና ቸር ነውና ምህረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ (2x) እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰው በከንቱ ይደክማል መሰረቱ ግን የሆነ ቤቱ ይጸናል ይቆማል ሁለትን ሰው አንድ የሚያደርግ ልዩ ችሎታ አለው ይህ ዕውቀቱ አሰራሩ ለእኛ እጅግ አስደናቂ ነው እድምተኞቻችን ብሉልን ጠጡልን ከሚሏቹህ ሌላ ቃል አላቸው ዛሬ አክብሩልን ብለው የጌቶቹን ጌታ ስንቱን አሳልፎ ቤት ለሰራላቸው ለዚህ መድሃኒያለም ከምሥጋና ሌላ የሚሰጠው የለም ከዕልልታ ሌላ የሚሰጠው የለም ከጭብጨባ ሌላ የሚሰጠው የለም ከዝማሬ ሌላ የሚሰጠው የለም አዝ፦ የወንድ ሙሸራ ድምጽ የሴት ሙሸራ ድምጽ ቸር ነውና ቸር ነውና ምህረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ (2x) የታመነ አምላክ በእራሱ መንገዱ ያስተሳሰራቸው ከአእምሮ በላይ በሆነው ጥበቡ ያገናኛቸው ከፀሐይ በታች ባገኙት በዕድሜ ዘመኖቻቸው ጌታ ይረዳናል እያሉ ጀመሩ ደስ እያላቸው ዛሬን የደስታ ቀን የጥምረት የሃሴት ንጉሥ ካደረገው ይህን አዲሱን ቤት ወዳጅ ቤተሰቦች አብረን እንመርቀው ሚስትን ያገኘ ሰው በረከት ካገኘ ሞገስ ከሆነለት እንዲህ ላደረገው ምሥጋና ይብዛለት እንዲህ ላደረገው ጭብጨባ ይብዛለት ይህን ላደረገው እስኪ ተቀኙለት ይህን ላደረገው ዕልልታ ይብዛለት አዝ፦ የወንድ ሙሸራ ድምጽ የሴት ሙሸራ ድምጽ ቸር ነውና ቸር ነውና ምህረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ ሙሽሮቹ ይላሉ (2x) ዛሬን የደስታ ቀን የጥምረት የሃሴት ንጉሥ ካደረገው ይህን አዲሱን ቤት ወዳጅ ቤተሰቦች አብረን እንመርቀው ሚስትን ያገኘ ሰው በረከት ካገኘ ሞገስ ከሆነለት እንዲህ ላደረገው ምሥጋና ይብዛለት እንዲህ ላደረገው ጭብጨባ ይብዛለት ይህን ላደረገው እስኪ ተቀኙለት ይህን ላደረገው ዕልልታ ይብዛለት ከምሥጋና ሌላ የሚሰጠው የለም ከዕልልታ ሌላ የሚሰጠው የለም ከጭብጨባ ሌላ የሚሰጠው የለም ከዝማሬ ሌላ የሚሰጠው የለም እንዲህ ላደረገው ምሥጋና ይብዛለት እንዲህ ላደረገው ጭብጨባ ይብዛለት ይህን ላደረገው እስኪ ተቀኙለት ይህን ላደረገው ዕልልታ ይብዛለት ከምሥጋና ሌላ የሚሰጠው የለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection