Song Lyrics

እንመርቃቸዋለ

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
በስመአብ ወወልድ ወመፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሄ ጋብቻ የተባረከ ጋብቻ ይሁንልን አሜን አዝ፦ አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ እንመርቃቹሃለን አሜን (6x) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (2x) ክርስቶስ እርሱ የሆነው መሰረት እራስ ሆኖ ይንገሥበት እዚህ ይግባልን??? ቸርነት ትዳሩም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የባርኮት ሽታ ሸቶ በምሳሌነት ተሞልቶ ከድግስ ያለፈ (አዎ) በሕይወታቸው ጉዞ (አዎ) ይምራቹህ እጃችሁን ይዞ አዝ፦ አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ እንመርቃቹሃለን አሜን (6x) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (2x) ቤተሰብ ጤናማ ቤተክርስቲያን ያድርጋት እንደብርሃን በፀጋው ብዛት ለማዳን የደስታ ምንጭ ሆኖ ይፍለቅለቅበት የተጠሙም የሚረኩበት ያዘኑም የሚደሰቱበት እግዚአብሔር አዘዘ (አዎ) ጋብቻ እንዲከበር (አዎ) ከጥንቱም ልክ እንደዚህ ነበር ቃልኪዳን አላቹህና ከእግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ተባልን የአምላካቹህ ባርኮት ነው ውለዱ ክበዱ ይሁን ደስታ በፍቅር አምላክ በጌታ በሕይወታችሁ አለኝታ እግዚአብሔር ያኖራል (አዎ) መኖሪያቹህ ሆኖ (አዎ) ማን አፍሯል በእርሱ ተማምኖ አዝ፦ አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ እንመርቃቹሃለን አሜን (6x) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection