Song Lyrics

የደስታ ቀን ነው

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
አዝ፦ የደስታ ቀን ነው ደስ እያለን (3x) የደስታ ቀን ነው ደስ ይበለን (3x) ቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የተገኘው ኢየሱስ ጌታችን ዛሬም አለ ብለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (2x) አንደ ቃና ገሊላ ጌታ ከተጋበዘ ለሰርጉ ብቻ ሳይሆን እንዲኖር ከታገዘ ኢየሱስ ያለበት ትዳር ሁሌ ይጣፍጣል ጨለማ ወደ ብርሃን ሁሌ ይለወጣል ፈጥኖ በታማኝ እጁ ባዶውን ይሞላል ጌታ ይኑርበት እንጂ ሁሉ ይባረካል አዝ፦ የደስታ ቀን ነው ደስ እያለን (3x) የደስታ ቀን ነው ደስ ይበለን (3x) ቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የተገኘው ኢየሱስ ጌታችን ዛሬም አለ ብለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (2x) መልካም ነው ያልውን ይኸው አሳይቶናል ለዚህ ላበቃቸው ክብር ይገባዋል ወግ ማድረጉ እዚህ መድረሱ መባረኩ መከናወኑ (2x) አሃሃሃ አዎ (3x) ከእግዚአብሔር ነው አሃሃሃ አዎ (3x) ከእግዚአብሔር ነው አዝ፦ የደስታ ቀን ነው ደስ እያለን (3x) የደስታ ቀን ነው ደስ ይበለን (3x) ቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ የተገኘው ኢየሱስ ጌታችን ዛሬም አለ ብለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (ሆሆሆ) እንዘምራለን (አሃ) ደስ እያለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection