Song Lyrics

ምሥጋና ለእግዚአብሔር

Bruktawit & Getayawukal
Enkuan Des Alachu
አዝ፦ ምሥጋና ለእግዚአብሔር ምሥጋና ምሥጋና ሁለቱን ሙሽሮች አንድ አድርጓልና ምሥጋና (2x) የደስታ ቀን ነው ዛሬ የድል ቀን ነው የዝማሬ እግዚአብሔር ስለረዳቸው ኑሮም መሰረተላቸው የፍቅርን ቤት ሰራላቸው ባሳለፉት ዘመናቸው መከራ እንኳን ቢገጥማቸው በዚያ ሁሉ አግዟቸው ከክፉ ሃሳብ ጠብቋቸው ዛሬ ለዚህ አበቃቸው አዝ፦ ምሥጋና ለእግዚአብሔር ምሥጋና ምሥጋና ሁለቱን ሙሽሮች አንድ አድርጓልና ምሥጋና (2x) በሶስትም የተገመደ አይበጠስ አይበጠስ ጌታ እስካለ ድረስ (4x) ተከናወነ ብቸኝነት ቀረ ጌታ ያስደስታል እያጣመረ እያስተሳሰረ (2x) አሃሃ ፊታቸው አሃሃ አላፈረም አሃሃ ጋብቻው አሃሃ ስመረ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection