አዝ፦ ቃል ብቻ ተናገር (4x) የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (3x) ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (3x) የታመመብኝን ሰው አልጋ ላይ አስተኝቼ ወደ አንተ መጣሁኝ ሁሉን ነገር ትቼ ቃልህ ዓይን እንዳለው ስለተማመንኩኝ መቅደስህ ገብቼ ቃልህን ጠበኩኝ ተነሳ ከአልጋ ላይ ብለህ እዘዝልኝ ወዲያው እንደሚነሳ በቃል አምናለሁኝ (2x) አዝ፦ ቃል ብቻ ተናገር (4x) የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (3x) ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (3x) ለሰው ያልነገርኩት ማንም የማያውቀው እንድ ጉዳይ አለኝ አንተ የምታውቀው አምላክ ይቻልሃል ለአንተ ሁሉ ነገር ለችግሬ መውጫ ስለአዘጋጀህ በር እስከመቼ ድረስ ልሸከም ጥያቄ ቃል ብቻ ተናግረህ ፍታ እንቆቅልሼን (2x) አዝ፦ ቃል ብቻ ተናገር (4x) የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (3x) ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (3x) እኔ የቀመስኩትን ሕይወት ያልቀመሱ በምስራች ወንጌል ገና ያልተደረሱ በቤቴ ሞልተዋል አንተን ያልተረዱ ወደ ሞት ጐዳና ዝምብለው ሚነዱ ዛሬ ቃል ተነገር እንዲለወጡልኝ ቤቴ ወንጌል ይግባ አንተን/ጌታን ያግኙልኝ (2x) አዝ፦ ቃል ብቻ ተናገር (4x) የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (3x) ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (3x) ሰማይና ምድርን በቃልህ አጽንተሃል ሁኑ ስትል ሆነው በአንተ ተፈጥረዋል ቃልህ ኃይለኛ ነው ስልጣን የተሞላ ሰይጣንን የሚጥል እሳት ነው ሚባላ በሕይወቴ ዘመን የሚያስቸግረኝን ቃል ብቻ ተናግረህ ጠላቴን/ሰይጣንን ጣልልኝ (2x) አዝ፦ ቃል ብቻ ተናገር (4x) የአንተ ቃል ተራሮችን ዘሎ ይመጣል (3x) ቃል ብቻ ስትናገር ያልከው ይሆናል (3x) ደረቁን ምድረበዳ ምን ተስኖት ይሞላዋል በአበባ ምን ተስኖት የጐደለንን ሁሉ ምን ተስኖት ያደርግልናል ሙሉ ምን ተስኖት ለእርሱ የሚያቅት የለም ይችላል እርሱ ዘለዓለም ሁሉንም ቻይ ነውና እናንግሰው በምሥጋና (2x) ምን ተስኖት (4x) ምን ተስኖት (4x) የሞተውን ሬሳ ምን ተስኖት እናያለን ሲያስነሳ ምን ተስኖት ለእኛ ያቃተን ሁሉ ምን ተስኖት ይቻለዋል በእርሱ ምን ተስኖት ኤልሻዳይ አምላክ ነውና የሚሳነው የለምና ምን ተስኖት እንበለው ድል የሚገኘው ያኔ ነው (2x) ምን ተስኖት (4x) ምን ተስኖት (4x) ምን ተስኖት (4x) ምን ተስኖት (4x)