ከዘመድ አዝማድህ ተለይተህ ውጣ የሚልን ድምጽ ሰምቶ በእምነት የወጣ [1] አብርሃም ዛሬ ግን መቶ ዕድሜ ሊሞላ አስር አመት ቀረው ሊሻገር እርጅናን [2] ሲዘገይ የተስፋው ቃልኪዳን ሲጠፋ ከአብርሃምና ሳራ ተሟጠጠ ተስፋ ሃሳባቸውን ሳቱ እስማኤልም መጣ [3] ለዛ ጻድቅ ሰው ቤት ሁከትን አመጣ ነገር ግን ለመቶ አንዲት አመት ስትቀር የሳራን ማህጸን አሰበ እግዚአብሔር [4] ይስሃቅ የተስፋው ልጅ ወዲያው ተወለደ የተስፋው ጨለማ ተወገደ (2x) [5] አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ቃል ምንም ቢዘገይም መፈጸሙ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ቃል ቢዘገይም እንኳን ፍሬ አለው በኋላ (2x) እስራኤላውያን ከነዓን እንዳይገቡ ጋሬጣ ሆነባቸው የእያሪኮ ግንቡ ቀንደ መለከትን በእጃቸው ይዘው በታላቅ ዝማሬ ሊነድሉት ቆርጠው ፍፁም ሳይሰለቹ ህዝቡና እያሱ የእያሪኮን ቅጥር ሊደረማምሱ ቆርጠው ተነስተዋል ዙረት ጀምረዋል ይኸው ሳይነደል ስድስት ቀን አልፎታል ግን ለመጨረሻ መዞር ጀምረዋል መለከት መንፋቱን ተያይዘውታል በዚህ ታላቅ ተስፋ እያሪኮን ሲዞሩ የእያሪኮን ቅጥር አፈረሱ (2x) አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ቃል ምንም ቢዘገይም መፈጸሙ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ቃል ቢዘገይም እንኳን ፍሬ አለው በኋላ (2x) ሃናም መካኗ ሴት ልጅን ያልወለደች ለብዙ አመታት ብዙ ያለቀሰች ሁልጊዜ ወደ አምላኳ የምታፈስ እንባ ከአስር ልጆች ሁሉ ያልተሻላት ባሏ [6] ወደ ቤተ መቅደስ ስትጸልይ ገብታ እንባዋን ስትዘራ ለላይኛው ጌታ ካህኑ ኤሊ ግን ሰካራም ነሽ አላት የልቧል ሰቆቃ መቼ ተረዳላት [7] አምላኬ ልጅ ስጠኝ ለአንተው ሰጥሃለሁ ይኸው ተንበርክኬ ቃልኪዳን እገባለሁ [8] እያለች በተስፋ ስትጠብቅ ሳትሰለች ሳሙኤልን . (1) . ወለደች (2x) [9] አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ቃል ምንም ቢዘገይም መፈጸሙ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ቃል ቢዘገይም እንኳን ፍሬ አለው በኋላ (2x) ማርያምና ማርታ ታላቅ ወንድማቸው እጅግ የሚወዱትም ያ መመኪያቸው አልዓዛር ታሞ አልጋ ላይ ተኝቷል መሞቱም አይቀርም ብለውም ሰግተዋል ቶሎ በአፋጣኝ መልዕክትን ሰደዱ ወዳጁን ኢየሱስን ሊያስጠሩ ወደዱ ግን የአላዓዛር ሀመም እያደረ ባሰ እዛው በተኛበት ወንድማቸው ሞተ ተስፋቸውን ቆረጡ ወስደውም ቀበሩት አራት ቀን አለፈ ዋሻ ውስጥ ጣሉት ግን በአራተኛው ቀን ያ ወዳጁ መጣ ሟችሁን ከሙት በሃል አወጣ (2x) አዝ፦ የተስፋው/የተስፋህ ቃል ምንም ቢዘገይም መፈጸሙ አይቀርም የተስፋ/የተስፋሽ ቃል ቢዘገይም እንኳን ፍሬ አለው በኋላ (2x)