Song Lyrics

ዮሴፍ በሕይወት አለ (Yos

Bruktawit & Getayawukal
Barkoten Likuterew
በእርጅና የወለድኩት ልጄ ሞቶብኛል አጥንቱን ሳያስቀር አውሬ በልቶብኛል ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንኩ እወርዳለሁ ስለ ዮሴፍ ልጄ ዝምብዬ አለቅሳለሁ ከልጆቼ ሁሉ ይልቅ እወደው ነበር ቀሚስ ገዝቼለት ያጌጠች በህብል አስተዋዩ ልጄ ዮሴፍ ዛሬ ጠፍቷል ከልብሱ በስተቀር ሥጋው ተቦጫጭቋል እነዛ ሁለት ህልሞቹን ስጠብቅ ነበር ልጄን ትልቅ ቦታ እንዳየው ሲከብር ዛሬ የልጄን መርዶ ሰምቼ አዝኛለሁ ሰዎች ቢያጽናኑኝስ እንዴት አጽናናለሁ ይልጆቼን ወሬ አምጣልኝ ብዬ እኔው ነኝ ያዘዝኩት በበረሃ ልጄ እራሴው ነኝ እኔው አውሬ ያስበላሁት የሕይወቱን ጽዋ በአንዴ ያስጨለጥኩት ኧረ ምነው ቢቀርብኝ ባይላክስ ኖሮ ደህና አየው ነበረ ዮሴፍ በእድሜው ከብሮ እናቱም ወንድሙን ስታምጥ ሞታለች ይህንንማ ብታይ ምንስ ትለኛለች እያለ ሲናገር ያዕቆብ በጣም አዝኖ በልጁ ዮሴፍ ሞት እጅግ ተጸጽቶ ልጁን የሚታደግ እግዚአብሔር አለና ዮሴፍ በሕይወት አለ ምስራች ተሰማ አዝ፦ እግዚአብሔር ታድጐታልና ዮሴፍ በሕይወት አለ እንደገና (2x) ሞተ ብለው አረዱት የምስራች አሉ ቃሉ ተፈጸመ ለዮሴፍ ሰገዱ የዮሴፍ ወንድሞች ዮሴፍን ሸጠዋል ግን ጌታ አክብሮት ሻጩን ያሰግዳል አዝ፦ እግዚአብሔር ዮሴፍን ወዶታል በወንድሞቹ ላይ አክብሮታል (2x) ያዕቆብ የእንባው ዘመን ዛሬ አበቃለት የዕድሜውም ፍጻሜ እልልታ ሆነለት የሃያ ብር ባሪያ ዛሬ ጌታ ሆኗል በምድረ ግብጽ ውስጥ ንጉሥ አክብሮታል አዝ፦ እግዚአብሔር ዮሴፍን ወዶታል በምድር ሁሉ ዙሪያ አክብሮታል እግዚአብሔር ታድጐታልና ዮሴፍ በሕይወት አለ እንደገና እግዚአብሔር ታድጐኛልና እኔም በሕይወት አለሁ እንደገና (2x) እግዚአብሔር ታድጐሃልና አንተም በሕይወት አለህ እንደገና እግዚአብሔር ታድጐሻልና አንቺም በሕይወት አለሽ እንደገና እግዚአብሔር ታድጐናልና እኛም በሕይወት አለን እንደገና(2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection