Song Lyrics

ፍቅርህ ትልቅ ነው

Bruktawit & Getayawukal
Barkoten Likuterew
አዝ፦ ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (2x) ጸሃፊ መች ጠፍቶ በምድር ላይ ምሁር ሰው የአንተን ታላቅነት ጀምሮ አይጨርሰው መች አንዲህ ይቀላል ስለአንተ ቢባል ቢባል ቢጻፍልህ ተጀመሮ ቀለም ያልቃል እኔ ግን አድናቆቴን ለአንተ ባለኝ በሰጠኸኝ ዜማ ማወደሴን ማክበሬን አልተውም ለፍጥረት ሁሉ እስኪሰማ ጌታዬ ጌታዪ ነህ እያለኩ ቤትህ ቆሜ እንጓደዳለሁ ኧረ ልዩ ነህ አንተ እኮ ለእኔ እንደአንተ የት አገኛለሁ አዝ፦ ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (2x) ስለአንተ ክብር ስልጣን ሞገስ ማንነት እየተረከ ነው ይኼ ሁሉ ፍጥረት ይህ ነው እስከዛሬ ከፍጥረት ጀምሮ አላለቀበትም ስለአንተ ተናግሮ አቤት ድንቅ ነህ አምላኬ እሄ ሁሉ ምሥጋናና ስግደት ያለማቋረጥ ያጐርፍልሃል ፍጥረት ሁሉ ከያለበት እኔም ተረኛ ነኝ ለአንተ ዛሬ ፊትህ ለማቅረብ ምሥጋና ጌታዬ ጌታዪ ነህ እያልኩኝ ልቀኝልህ እንደገና አዝ፦ ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (2x) እስከ ዛሬ ስለአረክልኝ ውለታ አቀርብልህ ነበር ምሥጋናና እልልታ ስለአረክልኝ አይደለም ምቀኝልህ ስለደነቀኝ ነው የአንተ ማንነትህ ተገረምኩ አድናቆት ያዘኝ በአንተ ማንነትህን አውቄ እስቲ ጌታዬ ጌታዬ ልበል በእግሮችህ ስር ወድቄ ቃላት ያንሰኛል ለመግለጽ የአንተን ማንነትህ ወደር የለው . (1) . ፍቅርህ ስምህ ምሥጋና ይድረሰው አዝ፦ ፍቅርህ ጥልቅ ነው (ጌታዬ) ምህረትህ ብዙ (ጌታዬ) ቸርነትህ አያልቅ (ጌታዬ) አንተ ታላቅ ነህ (ጌታዬ) ስራህ ግሩም ነው ጌታዬ ጌታዬ አንተ ነህ ባለውለታዬ/አንተ ልዩ ነህ ለእኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection