አዝ፦ ሰላም አለኝ (3x) በልቤ በልቤ ቅዱስ ቃሉን አንብቤ ደህንነት አግኝቻለሁ በጌታ ሰላም አግኝቻለሁ ሰላሜ በውስጤ እንዲህ የፈሰሰው ኢየሱስ በደሙ ሕይወቴን ገዝቶት ነው በጭንቅ ከመወጠር አዕምሮዬ ያረፈው እረፍት የሚሰጠው ጌታ ስላለኝ ነው ባይሆንማ ኢየሱስ ለእኔ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ባይገዛው ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ተይቬ ጉስቁልና ከቦኝ በስቃይ ተውጬ ነበረ የምገኝ ግን ጌታዬ ኢየሱስ እርሱ ስላለልኝ እረፍት አግኝቻለሁ ተፈትቻለሁኝ (2x) አዝ፦ ሰላም አለኝ (3x) በልቤ በልቤ ቅዱስ ቃሉን አንብቤ ደህንነት አግኝቻለሁ በጌታ ሰላም አግኝቻለሁ ልቤ መልካም ነገር እንዲህ ያፈለቀው የእግዚአብሔር ሃሳብ ሕይወቴን ሞልቶት ነው ልቤን ለእርሱ አርፎ ተዋርዶ የተገዛው እውነተኛ ፍቅሩን አውቆ ተረድቶት ነው ሕይወቴ ነው ነው ሰላሜ ነው ነው እረፍቴ ነው ነው አቅሜ ነው የምመካበት ሌላ ምን አለ ለእኔስ ኢየሱሴ ካለ ባይሆንማ ኢየሱስ ለእኔ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ባይገዛው ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ተይቬ ጉስቁልና ከቦኝ በስቃይ ተውጬ ነበረ የምገኝ ግን ጌታዬ ኢየሱስ እርሱ ስላለልኝ እረፍት አግኝቻለሁ ተፈትቻለሁኝ (2x) በጤንነት ሆኜ መውጣቴ መግባቴ ኢየሱስ ሆኖልኝ ነው ኃይልና ጉልበቴ ወደ መልካም ስፍራ እግሬ የሚሮጠው እግሬን የሚመራ ኢየሱስ ሆኖ ነው ሕይወቴ ነው ነው ፈዋሼ ነው ነው እረፍቴ ነው ነው አቅሜ ነው የምመካበት ሌላ ምን አለ ለእኔስ ኢየሱሴ ካለ ባይሆንማ ኢየሱስ ለእኔ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ባይገዛው ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ተይቬ ጉስቁልና ከቦኝ በስቃይ ተውጬ ነበረ የምገኝ ግን ጌታዬ ኢየሱስ እርሱ ስላለልኝ እረፍት አግኝቻለሁ ተፈትቻለሁኝ (2x) አቅሜ የእርሱን ስራ እንዴት ሊናገረው የእርሱ ውለታ በልቤ ሞልቶ ነው ልቤም መስቀሉ ስር ስለተዋረደ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጤ ነደደ ባይሆንማ ኢየሱስ ለእኔ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ባይገዛው ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ተይቬ ጉስቁልና ከቦኝ በስቃይ ተውጬ ነበረ የምገኝ ግን ጌታዬ ኢየሱስ እርሱ ስላለልኝ እረፍት አግኝቻለሁ ተፈትቻለሁኝ (2x) አዝ፦ ተለወጥኩኝ (3x) በኢየሱስ በኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ሆኛለሁ መንፈሱን አግኝቻለሁ በጌታ ለውጥን አግኝቻለሁ የእግዚአብሔር ማዳን ለሰው የማወራው ማዳኑን በዐይኔ ስለአየሁኝ ነው ሰዎችን ለመውደድ ለማፍቀር የቻልኩት በጌታዬ ፍቅር ስላገኘውሁ ነው እረፍት እረፍት አለኝ (3x) በኢየሱስ በኢየሱስ የማይጠፋ ደስታ የማይለወጥ ተስፋ በሕይወቴ በጣም ተስፋፋ ባይሆንማ ኢየሱስ ለእኔ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ባይገዛው ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ተይቬ ጉስቁልና ከቦኝ በስቃይ ተውጬ ነበረ የምገኝ ግን ጌታዬ ኢየሱስ እርሱ ስላለልኝ እረፍት አግኝቻለሁ ተፈትቻለሁኝ (2x) ሕይወቴ ነው ነው ፈዋሼ ነው ነው እረፍቴ ነው ነው አቅሜ ነው የምመካበት ሌላ ምን አለ ለእኔስ ኢየሱሴ ካለ