በበደል በሀጥያት ሙታን የነበርነው ከመንግስቱ ጠፍተን ተጨንቀን ላለነው ከኢየሱስ ጋር ህይወትን አገኘን በርግጥ ሞተን ነበር በፀጋው አዳነን ( 2x) አዝድነናል ድነናል በፀጋው ድነናል /3 በጠላት እስራት በጨለማ ሆነን መሄጃው ጠፍቶብን ተስፋ ቆርጠን ሳለን አርነት ሊያወጣን ስለኛ ቆሰለ ሞታችንን ሞቶ በህይወት አኖረን ( 2x) አዝድነናል ድነናል በፀጋው ድነናል /3 በርግጥ ሞተን ነበር በጌታ ድነናል የዘላለም ህይወት በነፃ አግኝተናል ክሳችንን ከኛ ከኛ ላይ ወስዶታል ማይጠፋውን ህይወት በነፃ አግኝተናል ( 2x)