Song Lyrics

ምክንያቱ

ባለፍኩበት በሄድኩበት በመንገዴ ሁሉ ከነበርኩባቸው አስጨናቂ ቀኖቼ ፀጋህ ምህረትህ እያገዘኝ ዛሬን አደረሰኝ አዝምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለመድረሴ ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ ( 2x) ከማህፀን ገና ሳለሁ በስሜ የጠራኸኝ ከልጅነቴ ጀምሮ መንገድ የመራኸኝ ከጥፋት ጎዳና ጠበከኝ ዛሬን አሳየኸኝ አዝምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለማየቴ ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ ( 2x) ከኔ የሆነ ከቶ ምንም የለም ሁሉ ባንተ ነው የሆነው ከኔ የሆነ ከቶ ምንም የለም ሁሉ ካንተ ነው የሆነው አዝምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለመድረሴ ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ ( 2x) ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection