Song Lyrics

መኖሪያዬ

መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ ነው በክንዶቹ ጥላ አርፋለሁ የሚያስፈራኝ ሁሉ ተወግዷል ህይወቴን በሰላም ሞልቶታል ( 2x) አዝየለም እንደ ጌታ የለም የለም እንደ ኢየሱስ የለም አይኖርም ዘላለም ( 2x) በሰማይ በምድር የለም የሚመስለው ፡ እግዚአብሔር እጅግ ልዩ ነው ( 2x) እንዲህ ነህ ተብሎ ማይገመተው ከሰው ልጅ እጅግ የላቀ ከፍም ያለ ነው አዝየለም እንደ ጌታ የለም የለም እንደ ኢየሱስ የለም አይኖርም ዘላለም ( 2x) የሞተውን ነገር ህያው ነው የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው ያለቀውን ነገር ይሞላል የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው ( 2x) እረኛውን አይቶ ንጉስ ነህ የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው/2 አዝየለም እንደ ጌታ የለም የለም እንደ ኢየሱስ የለም አይኖርም ዘላለም ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection