[ቁጥር 1] እሹሹ የለመደች ሀጥያት በአንቀልባ ያዘልኳት አመፅ እግር አብቅላ አይኔ አያት ብኩን ነፍሴን ልታመስ ልታፈርስ ልታርደኝ መጣች አባብላ በማር አፏ በደላይ ቃሏ በደል ኋላ ልወድቅ በሷ አጥቼው ነበር ነፃነቴን የህፃንነት ልብ ቅንነቴን ቀን የሰጠው ቅል ቀና ልቤን እንዳይሰብርብኝ ለትንሽ ለትንሽ አስመለጥከኝ ሽሽ እያልከኝ ስተሻሽ ልክ እንደጨው ሳልሟሽሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ [አዝማች] ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ [ቁጥር 2] ስነከፍ ተገኘሁ ከሲኦል አፍ እራሴን ሳሳንቅ ለሞት መዳፍ ቀን ቀጥሮ ቆሞ አንዲት ነፍሴን ሳይወስድብኝ ለቲኒሽ ለቲኒሽ አስመለጥከኝ ታዲጊዬ እግዚአብሔር 'ምትከብ ጋሻ በትር ምርኩዝህ አፅናኝ ላሻ እንደእናት ንስር የምትረብብ አቅሌን ብስት እንኳ የምትቀልብ ከገዛ እብደቴ ለትንሽ ከሀሳብ ጡዘቴ ለትንሽ ከምናብ ሽፈቴ ለትንሽ ከስጋ ሽንፈቴ ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ አስመለጥከኝ [አዝማች] ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ ለትንሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ አስመለጥከኝ ለትንሽ [ቁጥር 3] ማከም ለለመደ ቃልህ መሀሪ ሰፊ ትከሻህ ማረም ለተካረ ድምፅህ ቤቴ የኔ ጥገኛህ ተማሪ ልቤን ይዤ መጣሁ አስተምርልኝ ብዬ ልጅህን መስዬ ልማዴን ጥዬ የምሬን [መውጫ] ተማሪ ልቤን ይዤ መጣሁ አስተምርልኝ ብዬ አስተምርልኝ ብዬ ረቡኒ ተማሪ ልቤን ይዤ መጣሁ አስተምርልኝ ብዬ