Song Lyrics

አስተምረኝ እሺ ማለት

Astemiregn Eshi Malet

[ቁጥር 1] የፅድቄ አምላክ እንዳላልኩህ ታቦትህ ፊት እንዳልጨፈርኩ በቅን መንገድ እንዳልድሄኩ እረኛዬን አንተ አሳዘንኩህ ሁሌ መልካም ሁሌ ደጉን ሁሌ ታማኝ ሁሌ ምስጉን የሆንክ ጌታ ስበድልህ በራሴ አፈርኩ እንዴት ልይህ ጨለማ በጨለማ አይበራ አዳፋ ልብስ በእድፍ አይጠራ ፅድቅ በሀጥያት ስለማይሰራ የንስሀን ልብ ስጠኝ አደራ [ቁጥር 2] ለመሸፈን አንዱን ጥፋት ሰደራርት ሌላ ሀጥያት ልኡሌ አንደው አይተህ ምን አልከኝ ነገር አንተው ነህ የገለጥከኝ በቃ ማረኝ ልውደቅ ፊትህ ራሴን ልጣል ለትእግስትህ እንዳልደገመው አቅምን ስጠኝ እሺ ማለት አስተምረኝ ተው ስትልኝ መተው መልመድ ከነፍሴ ይልቅ ያንተን መውደድ የጨው አምድ ሆኜ እንዳልገኝ እሺ ማለት አስተምረኝ በቃ ማረኝ ልውደቅ ፊትህ ራሴን ልጣል ለትእግስትህ እንዳልደገመው አቅምን ስጠኝ እሺ ማለት አስተምረኝ [መውጫ] ሚሰበር ልብ ስጠኝ አደራ የእሺታ ልብ ስጠኝ አደራ እሺ ማለት አስተምረኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection