Song Lyrics

አስተምረኝ እንቢ ማለት

Astemiregn Enbi Malet

አይቀመስም የጣፈጠ ሁሉ ማር የተለወሰ መርዝስ ቢሆን ቅሉ ከልብ አይወዱ ወዳጅ ነኝ ስላሉ እየሳሙ ሚሸጡ አገር ምድሩን [ቁጥር 1] ላለመጠላት ላለመጣላት ከሰው ለማደር እራስን ፀሀይ እያለች እሺ ብሎ ማለት ፀሀዮዋ ስትጠልቅ በፀፀት መተኛት እንደውሀ ቅርፅየለሽነት እወደድ ባይ አድርባይነት እንዳይገዛኝ እንዳይወርስ የኔን ቤት አስተምረኝ ጌታ እንቢ ማለት አስተምረኝ እምቢ ማለት አስተምረኝ እምቢ ማለት አሻፈረኝ የለም ማለት አስተምረኝ እምቢ ማለት [አዝማች] አይቀመስም የጣፈጠ ሁሉ ማር የተለወሰ መርዝስ ቢሆን ቅሉ ከልብ አይወዱ ወዳጅ ስላሉ እየሳሙ ሚሸጡ ሀገርን ምድሩን ሞሉ [ቁጥር 2] በይሉኝታ ነፍሴን እንዳላጣ ለይሉኝታ ራሴን እንዳላጣ በይሉኝታ ሞገስህን እንዳላጣ አስተምረኝ ቅዱሱን እምቢታ አስተምረኝ ከእውነት ተቧድኖ አስተምረኝ ውሸት ላይ አስተምረኝ በራስ ጨክኖ አስተምረኝ ልክን ማስቀደም አስተምረኝ እምቢ ማለትን አስተምረኝ ጌታ እምቢ ማለት አስተምረኝ አዎ እምቢ ማለት ኦ ኦ ኦ ኦ ኦ [መውጫ] ስለማይበልጥ ስሜት ከእውነት ስለማይበልጥ ሰው ከህይወት አስተምረኝ እምቢ ማለት አስተምረኝ እምቢ ማለት አስተምረኝ እምቢ ማለት! አስተምረኝ እምቢ ማለት!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection