(መግቢያ) ትርትር የምትል ልብ አለችኝ ስለነገ በማሰብ ረፍት ነሳችኝ (ቁጥር 1) አላስቆመው ነገን ከመምጣት አቅም የለኝ ሚሆነው ለመግታት ፀሀይን ውጪ ብዬ አላዛት ነፍሴን በገዛ እጄ አልፈጠርኳት የነፍሴ አምላኳ እኔ ካልሁንኩ ምን አስጨነቀኝ ላንተ መስጠት እየቻልኩ የራሴ አምላኩ ራሴ ካልሆንኩ ምን አስጨነቀኝ ላንተ መስጠት እየቻልኩ (አዝማች) አስተምረኝ ዝም ማለት የጌታ ፍቃድ ይሁን ማለት አስተምረኝ እግዚአብሔር አለ ማለት አንተ ተማምኖ መተኛት አስተምረኝ ዝም ማለት የጌታ ፍቃድ ይሁን ማለት አስተምረኝ እግዚአብሔር አለ ማለት አንተ ተማምኖ መተኛት (ቁጥር 2) ተጨንቄ ከቁመቴ ክንድ አልጨምር ፀጉሬ አይነጣ ወይ አይጠቁር ነገ ለራሱ ይጨነቃል ዛሬ ያደረሰን ለነገ ያውቃል ተጨንቄ ከቁመቴ ክንድ አልጨምር ፀጉሬ አይነጣ ወይ አይጠቁር ነገ ለራሱ ይጨነቃል ዛሬ ያደረሰን ለነገ ያውቃል የዘላለም አምላክ ሆይ አንተን ታምኖ ሚል እፎይ ልብ ስጠኝ የዘላለም አምላክ ሆይ አንተን ታምኖ ሚል እፎይ ልብ ስጠኝ (አዝማች) አስተምረኝ ዝም ማለት የጌታ ፍቃድ ይሁን ማለት አስተምረኝ እግዚአብሔር አለ ማለት አንተ ተማምኖ መተኛት አስተምረኝ ዝም ማለት ለፍቃድህ ሁሉን መስጠት አስተምረኝ እግዚአብሔር አለ ማለት አንተ ተማምኖ መተኛት (መውጫ) እግዚአብሔር አንተ አትሳሳት ቀኝ ስትል ግራ እንዳያምራት ትርትር ምትል የልቤን አቅል ጌታ ምራልኝ በፀናች ምክር ቸሩ መምህር አስተምርልኝ